Translation is not possible.

#ዊትር #ሰላት ‼ ❶ ትርጉሙ

➠ ዊትር (وتر) የሚለው ቃል ጎዶሎ ቁጥር (odd) እንደማለት ነው ለምሳሌ 1; 3; 5; 7... የመሳሰሉ ቁጥሮች ዊትር ሲባሉ 2;4 ;6... የመሳሰሉ ቁጥሮች ደግሞ ሸፍእ (شفع) ይባላሉ

➠ በመሆኑም የዊትር ሰላት ማለትበነዚህ ጎዶሎ ቁጥሮች የሚያበቃ ሰላት ማለት ነው።

❷ ግዴታ ነው ወይስ ሱና ?

➠ ሀነፍዮች ዊትር ግዴታ ነው ይላሉ ነገር ግን ከማስረጃ አንፃር ስናየው ዊትር ግዴታ እንዳልሆነና ነገር ግን በጣም የጠነከረ ሱና የተወደደ ተግባር መሆኑን እንረዳለን።የአብዛኛዎቹ ኡለሞች አቋምም ይህ ነው

➠ ግዴታ እንዳልሆነ ከሚጠቁሙ ማስረጃዎች መሀከል የአሏህ መልእክተኛ ﷺ ግዴታ የሆኑ ሰላቶችን በሚያስተምሩባቸው አጋጣሚዎች አምስት ወቅት ሰላትን ሲጠቅሱ ዊትርን ግን አለመጥቀሳቸው ነው።

➠ ግዴታ ባይሆንም ግን በጣም የጠነከረ ሱና ነውና አንድ ሰው ሊተወው አይገባም።

ኢማም አህመድ እንዲህ ይላሉ፦

" ዊትርን ሰላትን የተወ ሰው መጥፎ ሰው ነው ምስክርነቱን ሊቀበሉት አይገባም "

❸ የሚሰገድበት ወቅት

➠ የዊትር ሰላት የሚሰገደው ከኢሻ ሰላት በሗላ ጀምሮ ሱብሒ አዛን እስኪል ድረስ ባለው ወቅት ነው።

ማስረጃውም የአሏህ መልእክተኛﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው።

((አሏህ በዊትር ሰላት አቆያቹ አሏህ ከሰላተል ኢሻ ፈጅር እስኪወጣ ድረስ አደረገላችሁ)) 📚ቲርሚዚ 425

❹ በላጩ ማዘግየት ነው ወይስ በጊዜ መስገድ?

➠ ለሊት እነሳለሁ ብሎ ለሚል ሰው ወደ ለሊቱ ማብቂያ ማዘግየቱ ይወደድለታል።

➠ ለሊት ላይ መነሳት ለሚከብደው ሰው ግን ሳይተኛ በፊት ዊትር መስገዱ ይወደድለታል።

ማስረጃው!

የአሏህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ማለታቸው ነው፦

" በለሊቱ መጨረሻ አልቆምም ብሎ የፈራ ሰው በለሊቱ መጀመሪያ ዊትር ያድርግ በለሊቱ መጨረሻ እቆማለሁ ብሎ ያለሰው በለሊቱ መጨረሻ ይቁም የለሊቱ መጨረሻ ሰላት የሚጣዱበት ነው በላጭም ነው))📚 ሙስሊም 755

❺ ትንሹ የዊትር ቁጥር ስንት ረከአ ነው

➠ አነስተኛው ዊትር አንድ ረከአ ነው

ማስረጃውም

የአሏህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ማለታቸው ነው፦

((ዊትር አንድ ረከአ ነው ከለሊቱ መጨረሻ))📚ሙስሊም 752

➠ በመሆኑም አንድ ሰው ሁለት ሁለት ረከአ እያደረገ የለይል ሰላትን የፈለገውን ያክል ከሰገደ በሗላ በመጨረሻ አንድ ረከአ ዊትር ይሰግዳል።

➠ ወይም ደግሞ ሌላ ምንም የለሊት ሰላት ሳይሰግድ አንድ ረከአ ዊትር ብቻ ቢሰግድም ይችላል።

❻ ሌሎች የዊትር አሰጋገዶች አሉ ?

አዎ እነሱም ፦

➀ ሶስት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል

➠ ሶስት ረከአ ሲሰግድ ሁለት አይነት አሰጋገዶች አሉ

አንደኛው: ሶስቱንም ረከአ አከታትሎ በመሀል ተሸሁድ(አተህያቱ) ሳይቀመጥ በመጨረሻ ላይ ብቻ አንድ ተሸሁድ ቀርቶ ያሰላምታል።

ሁለተኛው: ሁለት ረከአ ሰግዶ ያሰላምትና እንደገና አንድ ረከአ ሰግዶ ያሰላምታል።

➠ ሶስት ረከአ ሲሰግድ ከፍቲሀ በሗላ በመጀመሪያው ረከአ (( ሰቢህ ኢስመረቢከ)) የሚለውን ሱራ በሁለተኛው ደግሞ ((ቁልያ አዩሀል ካፊሩን)) በሶስተኛው ረከአ ደግሞ ((ቁልሁወላሁ አሀድን)) ቢቀራ ይወደድለታል።

➁ አምስት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል

➠ ተሸሁድ ሚቀመጠው በመጨረሻ ላይ አንዴ ብቻ ነው መሀል ላይ ምንም ተሸሁድ አይቀመጥም።

➂ ሰባት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል

➠ በዚህም ግዜ ተሸሁድ ሚቀመጠው በመጨረሻ ላይ አንዴ ብቻ ነው መሀል ላይ ምንም ተሸሁድ አይቀመጥም።

➃ ዘጠኝ ረከአ ዊትር መስገድም ይችላል

➠ በስምንተኛው ረከአ ላይ ተሸሁድ ይቀራና ይነሳል ከዛህም በዘጠነኛው ረከአ ተሸሁድ ብሎ በዛው ያሰላምታል።ሁለት ተሸሁድ ይቀራል ማለት ነው።

➠ በነዚህ ሁሉ የዊትር አሰጋገዶች ላይ ሀዲስ ስለመጣ አንድ ሰው የቀለለውን መርጦ መተግበር ይችላል።

➠ አንዱን አንድ ቀን ሌላውን ደግሞ ሌላቀን ቢጠቀም ይበልጥ ይወደድለታል።

❼ ቁኑት

➠ ቁኑት የሚባለው ዊትር ሰላት ላይ በመጨረሻው ረከአ ከሩኩእ ከተነሳን በሗላ ሱጁድ ሳኖርድ በፊት የሚደረግ ዱአ ነው።

➠ ዊትር ላይ ቁኑት የተወደደ ተግባር ነው ነገር ግን ግዴታ አደለም።

➠ አንዳንዴ እያለው አንዳንዴ ቢተወውም ችግር የለውም ዘወትር ቢለውም ችግር የለውም።

_____________________

Send as a message
Share on my page
Share in the group