Translation is not possible.

"የጋዛ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላል" አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ጦርነት ላይ እርምጃ እንዲወስድ በመጠየቅ የተባበሩት መንግስታት ቻርተር አንቀጽ 99 ተግባራዊ እንዲያደርግ በስልጣን ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጌዜ ይህን ትልቅ የሚባል አንቀፅ ጠቅሰው ደብዳቤ ፅፈዋል።

የዋና ጸሃፊው ብርቅዬ እርምጃ የመጣው የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤል ሐማስ እና በአጋሮቻቸው መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ የውሳኔ ሃሳብ ባቀረበበት ወቅት ነው። የተባበሩት መንግስታት በጣም ኃይለኛ አካል ተደርጎ የሚወሰደው 15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት የአለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት።

ጉቴሬዝ ለምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በፃፉት ደብዳቤ በእስራኤል እና በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች ያለውን ሁኔታ "ለአለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ስጋት ሊሆን ይችላል" እየተካሄደ ያለው ጦርነት በጋዛ ሰብአዊ መቅሰፍት የሚያመጣ ነው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ ይህንን እርምጃ ጠይቋል።

ለጉቴሬዝ ደብዳቤ ምላሽ የፀጥታው ምክር ቤት አባል የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አዲስ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ ማቅረባቸውን እና "የሰብአዊ የተኩስ አቁም ውሳኔ በአስቸኳይ እንዲፀድቅ ጠይቀቃለች"።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group