Translation is not possible.

📵ከሰው ተሸሽጎ ሁሉን ቻዩን ማመጽ

بسم الله الرحمن الرحيم

"ከእለታት ባንዱ ቀን" ይላሉ ታላቁ የኢስላም ሊቅ ሸይኽ ዐብዱ-ረዛቅ አል-በድር የአሏህን እይታ ከሰዎች አሳንሰን በድብቅ ጌታችንን ለምናምጽ ደካማ ባሮች ምክራቸውን ሊለግሱ የአንድን ግለሰብ የታሪክ ክስተት ሲያስታውሱ። "አንድ ግለሰብ ብቻውን ሆኖ ያጋጠመውን ክስተት ይናገራል። ይህን ሰው ነብሱ በዘመናችን ወደ ተበራከተው ወንጀል ክልክል የሆኑ videosን ወደ መመልከት ጠራችው። ሰውዬውም ጥሪውን ተቀበለ። ክፍሉንም ዘጋግቶ ጎኑን አልጋው ላይ አሳረፈ። በዚያው ቅጽበት ነበር ማንም ሊያየው እንደማይችል በመገመት Mobile ከፍቶ ወደ social media የገባው(ያ በአግባቡ ካልተያዘ የከረፋው ስፍራ)።የአሏህን እይታ ችላ በማለትም በ Social media አጸያፊ ነገራትን መመልከቱን ተያያዘው። ከቆይታ በኋላም በር ላይ ድምጽ ሰማ!!!(ማን ይሆን!?) በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ሆኖም ሁሉንም ነገር አጠፋፋና ወደ በሩ አመራ። ዳሩ ግን በሩን ሲከፍት የተመለከተው ያ የፈራው የሰው ልጅ ሳይሆን ድመት ነበረች በሩ ስር የነበረችው። "

ኢናሊላሂ ወዒና ዒለይሂ ራጂዑን‼️‼️ ሁሉን ቻይ የሆነው ኻሊቅ እይታ ሳያስፈራው ከመኽሉቆቹ እይታ ተሰውሮ አሏህን ያምጻል‼️ አሏህን ትቶ ባሮቹን ያፍራል!!... እኛስ ወገኖቼ!? ከሰው ስንገለል ጉዟችን አሏህን ወደ ማመጽ ወይስ ወደ ዒባዳ ነው!? የእጅ ስልካችንስ ቢሆን ስንት ሙሀረማት ይሆን ከሰው ሸሽገን ያስቀመጥንበት!? እኛም ዐዚዙ ማየት ሚሳነው መስሎን ይሆን⁉️ ላ ወሏህ‼️ ታግሶን ቢሆን እንጂ እርሱ ሁሉንም ይታዘባል። ነገር ግን ሊቀጣን አይሻምና ወደርሱ እንድንመለስ ሌት ተቀን ይጠራናል። ሱብሀነከ ረበና👌

👌 እናም እስቲ ራሳችንን እንፈትሽ!! ይህ ጸያፍ ተግባር ላይ ወድቀን ከሆነም ያማረ መመለስን ወደ አሏህ እንመለስ!! እርሱ ረህማን ሁሉንም መሃሪ የሆነ ጌታ ነውና።

አሏህ የተውበቱን መንገድ ገር ያድርግልን🤲🤲

✍Abu remzan

for more 👇👇

https://ummalife.com/aburemzan

aburemzan | UmmaLife

aburemzan | UmmaLife

aburemzan: aburemzan. Nikname: @aburemzan | One Ummah — One Network - was created as a response to the Internet technology needs of Muslims and all adherents of traditional value
Send as a message
Share on my page
Share in the group