Translation is not possible.

ምርጥ. ሚስት ..

አንድ. ሸይኽ እንዲህ አሉ

[ ብናውቅ ኖሮ በእናታችን ሆድ ውስጥ ሆነን መልካም ሚስት ስጠን ብለን እንለምን ነበር ብለዋል። ]

ተወልደን አድገን አልፎም ያገባው ስለመልካም ሚስት ዱአ ሊዘናጋ አይገባም።

ምድር ካስተናገደቻቸው ምርጥ ሚስቶች መሐከል፦

ዛሬ ባለትዳሮች መሐከል ይህ ድርጊት ታደርጋለች ተብሎ ባይታሰብም የነብዩ ባለቤት አይሻ

( አሏህ ስራዋን ይውደድላትና)

እንዲህ ነበረች ፦

[ የመልክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ልብስ እርጥብ

መንይ በነካው ጊዜ አጥብላቸው ነበር መንዩ ደርቆ ከሆነ

እፈቀፍቅላቸውና ይሰግዱበት ነበር ] ብላለች።

~ አይሻ ሳትጠየፍ ሳታፍር ሰርታ ያለፈችው ዛሬ በኢልም ማዕዶች ላይ ስለዚህ ርዕስ ሲወራ ወንዶችም

መሽሞንሞናቸው ሴቶች አይን አውጣ እባለለሁ ይሁን ብቻ አላውቅም ከሀቅ ያፍራሉ ።

~ አይሻ እድሜዋ ከ ነብዩ ሲጋቡ ዛሬ በሰፈራችን የሚጫወቱ ህጻን አይነት እድሜ ላይ ነበረች

~ አይሻ ውዱ ነቢይ ወደ አኼራ ሲሄዱ እድሜዋ 18 ዛሬ ለትዳር ለማጨት ስትጠይቅ እድሜዋ አልደረሰም ብለው

እንደሚሸኙ አይነት ነው

~ አይሻ ከ 9 እስከ 18 አመት ባለው እድሜዋ የመልክተኛው የጀርባ አጥንት ሆና አለፈች ዛሬ አላህ ያዘነላቸው ሲቀር በሆነ ባልሆነው የምትነዘንዝ በዝተዋል

~ አይሻ በዛች እድሜዋ የሰራቻቸው መልካም ስራዎች የተጎነጨችው ኢልም ዛሬ የእኛ እህቶች መሬት ወርደው

እንደ ሚዳቆ በገመድ ዝላይ እና ሰለጠኑ ከተባለ በቀለም አሸብርቆ በታኮ ጫማ ልታይ ባይነት ያሳስባቸዋል

~ አይሻ ከመልክተኛው ጋ ከአንድ ወር በላይ ቤታቸው እሳት ሳያቀጣጥሉ እንዲሁም የሚበላ አጥተው አሳልፈዋል የእኛ እህቶች ዱንያ ዘውታሪ መስሎዋቸው ይሁን ብቻ አላውቅም እቃ ቤት ውስጥ አስቤዛ ካልተከማቸ ይሉሃል

~ አይሻ ከነቢያችን ጋር ስታሳልፍ ተደራራቢ ብፌ፣ አረቢያ መጅሊስ፣ ዘመናዊ ማንኪያ፣ ጭልፋ ፣አልጋ እንዲ አይነት፣ፍራሽ ካልገዛህ አላለችም ዱንያ አላፊ መሆንዋን ተረድታ የነበረው የዘምባባ ኬሻዋን አበጃጅታ ይተኙበት ነበረ

~ አይሻ እንደ ዛሬ ቀለም ሰራተኛ መስለው ወጥተው ከሚታዩ ሴቶች በተቃራኒ ከደሳሳ ጎጆዋቸው መውጣት

አታስበውም ነበር የዛሬዎቹማ ኒቃብም ለብሰው ኒቃባቸው ከፍተው ሲመገቡ ካፌ ላይ ይታያሉ ___ከአይሻ ያለው

እርቀት !!

~ አይሻ የእኛ እናት የረሱል ሚስት. የትዳር ምርጥ ተምሳሌት

[ የነብዩ ሙሐመድ አለይሶላቱ ወደሰላም ምርጥ ሚስታቸው ነበረች ]

ልጠቅልለውና

ጥሩ ሚስት እያልክ ስትቦርቅ የመልክተኛው ባህሪ ሙሉ

ስብዕና ለሚስታቸው ምን አይነት እንደነበሩ ማወቅ

መልካም ሴት ከመፈልግ ይቀድማል ብዬ አምናለሁ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group