Translation is not possible.

ውዱ መልዕክተኛችን ﷺ በአንድ ሐዲሳቸው ላይ እንዲህ ብለው ነበር፦

«የኾነ ጊዜ ይመጣል ከኡመቶቼ መካከል 5 ነገርን የሚወዱ፤ አምስት ነገርን ደግሞ የሚረሱ ሰዎች ይመጣሉ። እነዚህ ሰዎች፦ይህንን ዱንያ ይወዳሉ፤ አኺራን ይረሳሉ። ገንዘብን ይወዳሉ የሒሳቡን ቀን ደግሞ ይዘነጋሉ። ፍጡርን ይወዳሉ ፈጣሪን ይረሳሉ። ሐጢያትን ይወዳሉ ተውበት ማድረግን ይረሳሉ። ቤተመንግስቶችን ይወዳሉ መቃብሮችን ደግሞ ይረሳሉ።» 😢

سيأتي زمان على أمتي يحبون خمسا وينسون خمسا، و يحبون الدنيا و ينسون الآخرة، ويحبون المال وينسون الحساب، ويحبون الخلق وينسون الخالق، ويحبون الذنوب وينسون التوبة، ويحبون القصور وينسون المقبرة

ተጨባጫችን ግን አያስፈራም? የተናገሩትን ዘመን እየኖርን አይመስላችሁም? ሁሉም ሰው የዲን አስተማሪውም ጭምር ገንዘብ፤ ገንዘብ ብቻ በሚልበት፡ ማህበረሰቡ ስለ ቤትና መሬት፤ ስለ መኪና እና ቢዝነስ ተጨንቆ በሚያወራበት ልክ ስለ ሰላትና ቁርዓን፡ ስለ አላህና ረሱለላህ በማያወራበት፤ አላህ ያወገዛቸውን ስራዎች በኩራት በምንሰራበትና ወደ አላህ መመለሻ መንገዱን በረሳንበት ተጨባጭ፡ መንፈሳዊ ጉዳዮችን የሚያዘወትረውን እንደ ፋራ፥ ከTrendኡ ጋር የሚጓዘውን እንደ አራዳ በሚቆጠርበት ሁኔታ ይህንን ሐዲሳቸውን ማስታወስ ግድ ይለናል!

አኺራን አርቀን ዱንያን አቀረብን። ጊዜያዊውን ወደን ዘላለማዊውን ዘነጋን። እና ምን ተሻለን? ደጋግመን ወደ አላህ በመመለስ፤ ወደ ኡለሞች በመጠጋት፤በመተናነስ፤ አላውቅም'ን በማዘውተር! የዘነጋናቸውን በማስታወስ! ጥገኝነታችንን ዱንያ ላይ ሳይሆን አላህ ላይ ብቻ በማድረግ! መውጫው መንፈሳዊነት ነው... አላህ ያግዘና! ያመላክተን 💚

@ናዲያ

Send as a message
Share on my page
Share in the group