Translation is not possible.

ከሰጋጆች ስህተት……

ኢማሙ እያሰገደ ይደርሱና "ተክቢረት አል_ኢኽራም (የመግቢያው ተክቢራ)" ሳያደርጉ ቀጥታ ወደ ሰላት መግባት።

ለምሳሌ፦

ልክ ሲደርስ ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ወይም ሱጁድ ላይ ሆኖ ያገኘዋል፤ ከዝያም ወደ ሰላት መግቢያው ተክቢር (ተክቢረት አል_ኢኽራም) ሳያደርግ "አላሁ አክበር" ይልና ወደ ሩኩዕ ወይም ወደ ሱጁድ ይደፋል። ይህ ካደረገ ሰላቱ ውድቅ ይሆንበታል።

ምክንያቱም፦

ተክቢረት አል_ኢኽራም በሌላ ሊተኩ ከማይችሉ የሰላት አርካኖች አንዱ ነው።

ስለዚህ፦

ወደ መስጂድ ስትደርስ ኢማሙ ሱጁድ ተደፍቶ ብታገኘው; ተስተካክለህ ትቆምና፣ እጆችህ አንስተህ "አላሁ አክበር" በማለት ወደ ሰላት ትገባለህ፣ ከዝያም ተክቢረት አል_ኢንቲቃል (የመሸጋገሪያ ተክቢራ) "አላሁ አክበር" በማለት ወደ ሱጁድ ትወርዳለህ።

የመጀመሪያው ተክቢራ ወደ ሰላት መግቢያ ሲሆን የሁለተኛው ወደ ሱጁድ መውረጃ ይሆናል።

ሌላም ቦታ ሆኖ ከደረስክ እንደዚሁ አድርግ።

ይህ ብዙሃን ሰጋጆች ዘንድ የሚስተዋል ስህተት በመሆኑ ልብ ልንለው ይገባናል!!

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group