Наган дахаан йохтахам.

ዱንያ

*

ቴሌቭዠን ሲመጣ ራዲዮኑን ጣልን፤ መኪና ሲመጣ በእግር መሄዱ ታከተን፣ ኢሜይል ሲመጣ ደብዳቤ መላላኩ ቀረ፣ በእጅ የምንስለዉን የልብ ቅርጽ በጣት ነክተን ዉዴታችን ገለጽን ❤️፡፡ እወዳችኋለሁ ❤️

ሞባይል ሲመጣ መጽሐፍ ማንበብ ሰለቸን፣ ሶሻል ሚዲያው ሲመጣ መዘያየሩ ቀረ፣ ቅድም ኦንላይን አይቼህ ነበር እኮ ተባባልንና አብሮ ዉሎ እንዳደረ ሰው ችላ ተባባልን።

ፌስቡክና ዩ ትዩብ ሲመጡ ከዕውቀት ይልቅ ወሬና መረጃን መረጥን፣ ኮምፒዩተር ስንገዛ እስክሪብቶ መጨበጥ ከበደን፣ ባንክ ሲያድግ እጅ በእጅ መገበያየት ቀረ፣ ሽቶ ሲመጣ የአበባ መዓዛው ጠፋን፡፡

ዱንያ እንዲህ ይዛናለች ..

ጊዜው የሩጫ ሆኗል፣ ዓለም የጥድፊያ ሆናለች፡፡ አንዱ ሌላዉን እየጣለ ወደፊት ገሰገስን።

ስንሞት ገንዘባችን ባንክ ዉስጥ ይቀራል፣ አላህ ያለለት ወራሽም ይወርሰዋል፡፡

አንድ ቻይናዊ ባለሀብት ሞተና ሚስቱ 1.9 ቢለዮን ዶላር ወረሠች አሉ፡፡ ብዙም ሳትቆይ ሾፌራቸው የነበረዉን ሰውዬ አገባች፡፡

ሾፌሩ እንዲህ ይላል - “ሁሌም ይሰማኝ የነበረው አለቃዬን እንደማገለግል ነበር፤ ነገር ግን አለቃዬ ለኔ ሲሠራ ነበር ለካ፡፡”

ዐጂብ የዱንያ ነገር!

አንባቢዎች አሸናፊዎች ናቸው።

አንብቡ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group