የኛ ሃገር ባንኮች‼
=============
(ደሃን በጣም ደሃ አድራጊዎች፣ ባለ ሃብትን በጣም ባለ ሃብት አድራጊዎች!)
||
✍ ሚስኪኑ ወገኔ ሆይ! ዛሬ ባንኮች እንደት እንደሚቀፍሉህ ልጠቁምህ ወደድኩ።
ይህን የባንኮች አሠራር ምናልባት ከፊሎች ከናካቴው አያውቁትም፣ ከፊሎች አስተውለውት አያውቁም፣ ከፊሎች ቢያውቁትም አማራጭ ስለሌላቸው ውስጣቸው እየጨሰ ተላምደውት እየኖሩ ነው።
ባንኮች በየመንገዱ አስቁመውህ በ10 ብርም ቢሆን አካውንት ክፈት የሚሉህ ለአንተ አስበው ይመስልሃል? «ፎቶ አልያዝኩም!» ስትላቸው እንኳ «ችግር የለውም፣ ሌላ ጊዜ ታመጣለህ!» ይሉሃል። ሽል ለማለት ብለህ «አካውንት አለኝ!» ስትላቸው ሊያስምሉህ ይደርሳሉ።
✔ ባንኮች እንደት መሰለህ የሚሠሩት። ከአንተ በትንሹ 10 ብር ወሰዱ። እንዳንተ ያሉ 20 ሚሊዮን ሚስኪኖች አሉ። ስለዚህ ከእናንተ ስንት ሸቀሉ? 200 ሚሊዮን ብር! አስበው ከአንዳችሁ ኪስ የወጣው 10 ብር ስለሆነች ምንም ላትመስላችሁ ትችላለች።
ከፊሎቹ በየወሩ ከሚያገኟት ደመወዛቸው ላይ ቀንሰው ያገኟትን ያጠራቅማሉ። ባለ 10 ሺህ ብር ደመወዝተኛ ለቤት ኪራይ 5 ሺህ ብር፣ ለምግብና ተያያዥ ወጪዎች 3 ሺህ ብር አወጣና ቀሪዋን 2000 ብር ባንክ አስቀመጠ። ከ124+ ሚሊዮን ዜጎች መካከል እንደዚህ አይነት 10 ሚሊዮን ዜጎች ቢኖሩ፤ ከነዚህ ብቻ 20 ቢሊዮን ብር ይቀፈላል። አስበው! ከፊሎች በ10 ሺዎች፣ በመቶ ሺዎች፣ በሚሊዮን የሚያጠራቅሙ አሉ። የነርሱን ስንጨምረው አስበው።
የሚገርመው ይሄ ከሁላችንም የተሰባሰበ ገንዘብ የሚውልበት አላማ ነው።
ይሄ ከየሚስኪኑ የተጠራቀመ ገንዘብ ለባለሃብቶች በብድር መልክ ይሰጥና ቢዝነስ ይሠሩበታል። አንተ ሚስኪኑም ከአንተና መሰሎችህ በተሰባሰበው ከተከፈተወረ ቢዝነስ ከፍለህ ትጠቀማለህ። አስበው! በአንተው ብር ትርፍ ሲሠራብህ! አያምም?
*
√ የሚገርምህ አንተ መኪና ወይም ቤት ለመግዛት አስበህ በወቅቱ ያለው አንተ የምትፈልገው መኪና ዋጋ 1 ሚሊዮን ብር ቢሆንና የምትፈልገው ቤት ግምቱ 10 ሚሊዮን ብር ቢሆን፤ አንተ ለጊዜው ያለህ ለመኪና 800 ሺህ ብር ቢሆንና ለቤቱ 8 ሚሊዮን ብር ቢሆን፤ በቃ የአመት ገቢዬን አጠራቅሜ ቀጣይ አመት እገዛዋለሁ ስትል፤ አንተ እያጠራቀምከው ያለውን ገንዘብ ተጠቅመው እየነገዱበት ያሉት ከባንኩ ጀርባ ያሉ ባለሃብቶች ኑሮን አስወድደውት ያ ቀጣይ አመት ልታገኘው የተመኘኸው መኪና 1.5 ሚሊዮን ብር ሆኗል፣ ቤቱ 20 ሚሊዮን ብር ገብቷል። አሁንም ቀጣይ አመት ስትል በየጊዜው እየጨመረ እነርሱ ወደፊት እየሸሹህ፣ አንተ ከኋላ እየተከተልክ አባራሪና ተባራሪ ሆናችሁ እድሜህ ይገፋና አንድ ቀን ሞት ይመጣል።
ግን ራስህን እየጎዳህ ያለኸው አንተ ነህ። ኑሮን ለሚያስወድዱብህ ባለሃብቶች ከየትም ተሯሩጠህ ገንዘብ ፈልገህ በባንክ በኩል ታቀብላቸዋለህ።
አንዳንድ የግል ባንኮችማ አክሲዮን ብለው በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ይሰባሰቡና ከየቦታው አጠራቅመው ለራሳቸው ተከፋፍለው ይነግዱበታል። ይሄ ህዝብ ብዙ ያልገባው ነገር አለ።
እነዚያ ባለሃብት ተብዬዎች ግን ያላለቀ ህንፃቸውንና አሮጌ መኪናቸውን መያዣ አድርገው ያንተን ብር ተበድረው ይሠሩበታል። አንተ እንደነርሱ ተበድረህ እንዳትሠራ ቤትና መኪና የለህም። በቃ እንዲህ ሆነህ ውለታህ እንኳ ሳይቆጠር ማንንም ጠቃሚ ትሆናለህ።
*
√ ይሄ ይገርምሃል እንደ! ጭራሽ የወለድ ባንኮች ላይ ከወለድ አልባ በሚባለው መስኮት የሚያጠራቅም ሙስሊም አለ። እኔ'ምልህ ሐቢቢ! በዛ መስኮት የሰጡህ ብር ወለድ ካለበት መስኮት ላለመምጣቱ ምን ዋስትና አለህ? ሲጀመር እነርሱስ እንደት ብለው መቆጣጠር ይችላሉ?
ወይንስ የአንተ ከወለድ ነፃ ብሮች የተለዬ መልክ ስላላቸው እነዛን ለይተው ይስጡህ?
አትሞኝ! ንግድ ባንክ ከወለድ አልባ ያገኘውን ገቢ ዘምዘምና ሒጅራ ተደምረው አላገኙትም።
ቢያንስ ለሙስሊሞቹ ባንኮች ብትሰጣቸው ይበልጣል። ወንድሞችህ ይጠቀሙበት።
★
√ ምን ይሻል? ባንኮች አነስተኛ ገቢ ያለውንም ማኅበረሰብ ያማከለ ጥቅም እስኪዘረጉ ድረስ መታገል ግድ ነው። ሲጀመር የባለ ወለዶቹ እንደዛ ቢዘረጉም መጠቀም የለብንም። ከነርሱ ከናካቴው ውጡና ወደ ኢስላማዊ ባንኮች ዙሩ። ግን እነርሱም ጋ ገንዘባችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት።
እስኪ ሃሳብ አንሱና እንወያይበት። በተለይም መፍትሄው ላይ!
||
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.