Translation is not possible.

🚫::::::::የቂያም ቀን::::::::::🚫

☞ 3 ስራዎች ከትልቅነታቸው የተነሳ ሚዛን ላይ አይገቡም።✍

1) ☞ለሰዎች ይቅርታን ማድረግ ( ﺍﻟﻌﻔﻮ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﺎﺱ )

ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..

አላህ ﷻ እንዲህ ይላል ...

* ﻓَﻤَﻦْ ﻋَﻔَﺎ ﻭَﺃَﺻْﻠَﺢَ ﻓَﺄَﺟْﺮُﻩُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪ*ِ

" ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው... "

2) ☞ሰብር ( ﺍﻟﺼﺒﺮ ) ትግስት

* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..

አላህ ﷻ እንዲህ ይላል ...

* ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻳُﻮَﻓَّﻰ ﺍﻟﺼَّﺎﺑِﺮُﻭﻥَ ﺃَﺟْﺮَﻫُﻢ ﺑِﻐَﻴْﺮِ ﺣِﺴَﺎﺏٍ *

"❥ታጋሾች ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው።"

3) ፆም ( ﺍﻟﺼﻴﺎﻡ)

ረሱል ﷺ አሉ

አላህ ﷻ እንዲህ አለ -:

* ﻛﻞ ﻋﻤﻞ ﺍﺑﻦ ﺁﺩﻡ ﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﺼﻮﻡ ﻓﺈﻧﻪ ﻟﻲ ﻭﺃﻧﺎ ﺃﺟﺰﻱ ﺑﻪ .*

"ሁሉም የአደም ልጅ ስራ የርሱ ነው ከፆም በስተቀር ፆም የኔ ነው እኔም ነኝ ምንዳውን የምመነዳው ።"

{ ቡኻሪና ሙስሊም }

* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..

የቂያም ቀን ተጣሪው የታሉ ምንዳቸው በአላህ ላይ

የሆነው ሲል ይጣራል ...

❥ ፆመኞች

❥ታገሾችና

❥ ይቅር ባዮችን ብቻ ይቀበላቸዋል።

እኔንም እናንተንም በዚህች ጥሪ ከሚጠሩት አላህ ያርገን! አሚን🤲

"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ከዕለታት አንድ ቀን እቺን ምድር ለቅቀው ወደማይቀረው አኸይር መሄዴ አይቀርም ሞት ሐቅ ነው ለማንም አይቀርም ድንገት ይመጣል

Send as a message
Share on my page
Share in the group