Translation is not possible.

➧በቁርኣን ተጠቃሚ ለመሆን !

ቁርኣን ለሰው ልጆች መድህን ይሆን ዘንድ አላህ ከሰባት ሰማይ ከዐር በላይ በጅብሪል አማካኝነት በነብዩ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - ላይ ያወረደው የሁለት ሀገር ስኬት የያዘ የልብ መድሃኒት ተግፃፅና ብስራት እንዲሁም ዛቻና የተስፋ ቃል የያዘ መለኮታዊ የሕይወት መመሪያ ነው

ይህ ቁርኣን ማን እንደሚጠቀምበት አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ሲል ይገልፅልናል

" በዚህ ( በቁርኣን ) ውስጥ ለእርሱ ልብ ላለው ወይም እርሱ በልቡ የተጣደ ሆኖ ( ወደሚነበብለት ) ጆሮውን ለጣለ ( ለሰጠ ) ሰው ግሳፄ አለበት " ::

ሱረቱል ቃፍ : 37

በዚህ አንቀፅ በቁርኣን ተጠቃሚ ለመሆን አራት ነገሮች መሟላት እንደሚያስፈልግ አላህ ይነግረናል እነሱም :-

ተፅኖ የሚፈጥር ነገር

ተቀባይ ( የተፅኖ ማረፊያ )

መስፈርት

ከልካይ ነገር መወገድ

ተፅኖ ፈጣሪ ------ ቁርኣን ( ግሳፄ )

ተቀባይ ------ ልብ ( ሕያው የሆነ )

መስፈርት -------- ጆሮ መስጠት

ከልካይ ነገር መወገድ ---- ልብ ሌላ ቦታ አለመሄድ

ቁርኣን ተፅኖ የሚፈጥረው ሕያው በሆነ ልብ በተጣደ ጆሮ ሁለመናውን ወደ ቁርኣን አድርጎ ልቡ ከሸፈተበት መመለስና በቁርኣን ላይ እንዲሆን ማድረግ በቻለ ሰው ላይ ነው

በሱረቱ ያሲን : ከ69 - 70 ላይ አላህ እንዲህ ይላል " ይህ ቁርኣን ግልፅ ግሳፄ እንጂ ሌላ አይደለም :: ሕያው ለኾነ ሊያስጠነቅቅ " ::

ሰለዚህ በቁርኣን ተጠቃሚ ለመሆን እነዚህ አራት ነገሮች አሟልቶ መገኘት ያስፈልጋል

አላህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን።

Send as a message
Share on my page
Share in the group