Translation is not possible.

ስፔይን እስራኤልን ወራሪ ሀገር በማለት አወገዘቻት።

እስራኤል ከስፔን አምባሳደሯን ጠርታለች

ስፔይን ከአውሮፓ ሀገራት ሁሉ ቀድማ ከፍልስጥኤማውያን ጎን ተሰልፋለች ።

ፖለቲከኞቿ እስራኤልን ከማውገዝ አልፈው አለምአቀፍ ንቅናቄ ጀምረዋል !

የስፔይኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እስራኤል የፍልስጤም ምድርን ወርራለች ሲሉ ወርፈዋታል ።

እንደ አውሮፓ ሞራል አለን የምንል ከሆነ ከፍልስጤማውያን ጎን መቆምና የእስራኤልን ድርጊት ማውገዝ አለብንም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።

የስፔይኑ መሪ አክለውም ብቸኛው መፍትሄ ፖለቲካዊ ነው ያሉ ሲሆን ይህም የሚሆነው ፍልስጤም ሀገር ሆና ስትቆም ነው ብለዋል ።

ጠቅላይ ማኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ አውሮፓ ለፍልስጥኤም የሀገርነት እውቅና መስጠት አለባት ያሉ ሲሆን ስፔይን በበኩሏ ይህንን እንደምታደርግ ፍንጭ ሰጥተዋል ።

በጋዛ የሚደረገው የህፃናት ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን የተናገሩት የስፔይኑ መሪ ይህም እስራኤል አለምአቀፍ ህጎቾን የማታከብር መሆኗን ያሳያል ብለዋል ። በዚህ ድርጊት የተበሳጨቺው እስራኤልም አምሳደሯን ከስፔን ጠርታለች ።

ከቀናት በፊት የስፔይኗ ውብና ትልቅ ከተማ ባርሴሎና ከእስራኤል ጋር የሚደረግን ግንኙነት ሁሉ ማገዷ ይታወቃል ።

ስፔይን የአውሮፓዋ ደቡብ አፍሪካ ሆናለች !

Send as a message
Share on my page
Share in the group