Translation is not possible.

#አስቂኝ_ቂሷ

አንዱ ነው። የሆነችን ሴት ማጨት ፈልገ። ነገር ግን ዉስጡ ሙሉ በሙሉ አልተቀበላትም። ልጫት ወይስ ትቅርብኝ የሚል ሃሳብ ይመላለስበታል። ይሄን ዉስጣዊ ውዝግቡን ለማስተካከል  ቁርአን ልክፈትና መጀመሪያ ዐይኖቼ ባረፉበት አንቀጽ መልእክት ላይ  በመመስረት ዉሳኔ እወስናለሁ ብሎ ወሰነ። በዚሁ መሰረት ቁርአኑን በእጆቹ ያዘና ከፍተው። ሱረቱል ጣሃ ነበር የተከፈተው። መጀመሪያ አይኖቹ ያረፉባት የጌታችን ቃልም

"خذها ولا تخف"

የሚለው ነበር። "ያዛት። ምንም አትፍራ። የሚል ነው ትርጉሙ። አትፍራ!! ያዛት የሚለውን ቃል በማየቱ ተደስቶ ለማጨት ወሰነ። ግለሰቡ በአንድ ነገር ግን ተሸውዷል። እሱም ይች የምትያዘው ነገር ምንድን ነች የሚለውን አለማስተዋሉ ነው።

#እባብ ነች።

ሸይኽ ሷሊህ አል ዑሶይሚ

Send as a message
Share on my page
Share in the group