Translation is not possible.

🛑አልቃሳም ብርጌዶች

የዛሬው ውሏቸው:–

♦️የአሽቀሎን፣ የቤርሳቤህ እና የስዴሮት ከተሞች በበርካታ ሚሳኢሎች እና ሮኬቶች መተናል ብለዋል።

♦️አገዛዙ የጋዛ ጦርነትን እንደገና በቀጠለበት ወቅት የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ በእስራኤሏ ረኢም የጦር ሰፈር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀማቸውን ገለፁ።

♦️ኪሱፊም ከተማን በበርካታ ሚሳኤል መደብደባቸውንና በማዕከላዊ ክልል ሰማይ ላይ ሲበር የነበረ የጽዮናዊ ስካይላርክ ሰው አልባ አውሮፕላን መተው መጣላቸውን ገልፀዋል፡፡

♦️ከጋዛ ከተማ በስተሰሜን በኩል በርካታ ወታደሮችን ጭኖ ሲሄድ የነበረ የጦር ተሸከርካሪን በ"ታንዱም" መሳሪያ ኢላማ በማድረግ አጥቅተናል ብለዋል።

♦️በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኘውን የጠላት ታንክ በሻዋዝ ቦምብ ኢላማ አድርገን አውድመናል ብለዋል።

♦️በሰሜን ምዕራብ ጋዛ የሚገኝ ጠላት ጦር ላይ በ 114 ሚሜ "ራጁም" ሚሳኤል ስርዓት እና የሞርታር መሳሪያዎች ድብደባ መፈፀሙን አስታወቀ።

♦️በኔትዛሪም አከባቢ ላይ በሰፈሩት የወረራዋ ጦር ወታደሮች እና ተሽከርካሪዎች ላይ በርካታ የሞርታር መሳሪያዎችን በመጠቀም ድብደባ ፈፅመናል ብለዋል፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group