Translation is not possible.

ኢብኑ አባስ (ረዲዬ አላሁ አነሁም) እንዳስተላለፉልን ፡-

"የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሁለት አድስ በተቀበሩ ቀብሮች አጠገብ አለፉ፡፡

ከዚያም ረሱል "እዚህ ቀብር ውስጥ ያሉ ሰወች እየተቀጡ ነው አሉ፡፡ የሚቀጡትም በትልቅ ወንጀል አይደለም አሉ፡፡

የሚቀጡበት ምክንያት አንድኛው ሽንቱን በሚሸና ጊዜ ከጨረሰ በኃላ በደንብ አይፀዳዳም (አይጠርግም ወይም ስቲንጃ አያደርግም ነበር) ሽንቱ ልብሱን ይረጨው ያበላሸው ነበር አሉ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ የተንኮል ወሬን ከአንዱ ለአንዱ ሰው ያሰራጭ እና ያበጣብጥ ነበረ አሉ፡፡፡፡"

ከዚያም ረሱል የዘንባባ ቅርንጫፍ አምጡልኝ አሉና ለሁለት ከሰነጠቁት በኃላ በሁለቱም ቀብሮች ላይ ተከሉባቸው፡፡ ከዚያም ነብዩ (ሰዐወ) እንዲህ አሉ፡- እኚህ የዘንባባ ቅርንጫፎች እስኪደርቁ ድረስ የተወሰነውን ቅጣት ይቀንሱላቸዋል አሉ ነብዩ መሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም፡፡

#አላህ_ከቀብር_ቅጣት_ይጠብቀን፡፡፡፡

(ሀዲሱን ሙስናድ አህመድ በ1980 ላይ በሰሂህነት ዘግበውታል)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group