Translation is not possible.

የገጣሚ መከራ…

"አቡ ነዋስ" የሚባል ታዋቂ ገጣሚ ነበር። በጊዜው የነበረው አሚር የሆነች ግጥም ይፅፍና ለአቡ ነዋስ ያስጠራዋል። አቡ ነዋስ የአሚሩ ጥሪ ተቀብሎ መጣ።

አሚሩ……

"የፃፍኳትን ግጥም ገምግምልኝ" ብሎ ግጥሙን አነበበለት።

አቡ ነዋስ የአሚሩ ግጥም ከሰማ በኀላ

"ምንም ዓይነት የግጥም ሽታም የለውም" አለው።

አሚሩ ተናዶ

"ውሰዱና በአህያዎች በረት ለ1 ወር እሰሩት" አላቸው።

ከወር በኋላ……

"መልሳችሁ አምጡት" አላቸውና ድጋሚ ሌላ ግጥም ፅፎ አነበበለት። ልክ አንብቦ ሲጨርስ አቡ ነዋስ ሊወጣ ተነሳ።

አሚሩ አስቆመውና……

"የት ልቴድ ነው?"

ሲለው

"ወደ አህዮቹ በረት"

Send as a message
Share on my page
Share in the group