አንብቡ እንግዲህ ከዛ ግን አስተያየታችሁን አትንፈጉን 🙏🙏
ስለምን ከበደን...
ከእለታት አንድ ቀን...
የ ምእመናን እናት አኢሸቱል ኩብራ,
ነብዬን አይታቸው....
በደስታ ተሞልተው ፊታቸው ሲያበራ...
ደስታዎን አየሁኝ አንቱ ያላህ ወዳጅ,
እስቲ ዱዓ አርጉልኝ ድልን እንድቀዳጅ...
ስኬታማ እንድሆን በሁለቱም ዓለም,
ካንቱ ዱዓ በላይ ደጋፊ ኃይል የለም...
ብላ በትህትና ጥያቄ አቀረበች,
የአይኖቹአን ማረፊያ በስስት እያየች...
ታላቁ ነብይም ዱዓ አደረጉላት,
አላህ ሆይ ጌታዬ ለአኢሻ ማራት,
ወንጀሏን በሞላ...
በሁለቱም ዓለም ሚስቴን ደስ እንዲላት,
በድብቅም በግልፅ የፈፀመችውን,
በወንጀል መዝገቧ ያስቀደመችውን...
ወንጀሏን በሙሉ ማርልኝ ጌታዬ,
በርሷ ውስጥ አለና ሳቅ እና ደስታዬ...
ዱዓውን ስትሰማ የምእመናን እናት,
ደስታዋ ገንፍሎ ጮቤ አስረገጣት...
በደስታ ሰከረች ሳቀች ፈነደቀች,
በደስታዋ ብዛት ጭኗ ላይ ወደቀች...
አንቺ አኢሻ ሆይ እንዲህ ያስደሰተሽ,
ዱዓየ ነው እንዴ ጮቤ ያስረገጠሽ,
ብለው ቢጠይቁአት አኢሻ መለሰች...
እንዴት አልደሰት እንዴትስ አልፈንድቅ,
በአንቱ ዱዓ ጉልበት ከጀሃነም ስርቅ...
እንዴት አይኖር ስኬት...
እንዴት አይኖር ደስታ,
አንቱ ዱዓ አድርገው...
የዱዓው ተቀባይ ሆኖ ያንቱ ጌታ...
እንግዲህ ይግረምሽ ውዷ ባለቤቴ,
ለትልቅ ትንሹ ለሁሉም ኡመቴ,
ይሄ ነው ዱዓየ በአምስቱም ሰላቴ...
ብለው ተናገሩ...
ሀቢቡ ረሱሉ...
ጉድ አትልም? ወንድም...
አትገረሚም ወይ ውዲቷ እህቴ,
ለኚህ ታላቅ ነብይ ይሰዋ ሕይወቴ,
ፊዳ ይሁን ለርሳቸው ደም እና አጥንቴ...
በቀን አምስት ጊዜ...
በየ ሰላታቸው በዱዓ እያወሱን,
በዱዓቸው ብርታት...
በወደቅን ጊዜ ደግፈው እያነሱን...
ሱናቸውን መኖር ያዘዙትን መስራት,
ስለምን ከበደን ስማቸውን ማውሳት...
ሱናቸውን ማክበር እንደዞሩት መዞር,
ስለምን ከበደን እንደርሳቸው መኖር...
ጥዋት ማታ እያነሱን በውዱ ዱዓቸው,
ምን ያህል ጠፍተን ነው,
እኚን ታላቅ ነብይ ዛሬ የረሳናቸው...
አላህ ይመልሰን ወደመንገዳቸው,
በፍቃዱ ይጥቀመን በያኔው ዱዓቸው,
ጠንካራ ያድርገን ያፅናን በሱናቸው...
ሰለላሁ አለይህ ወሰለም ♥️♥️
አሚንን ♥️♥️