Translation is not possible.

~~~የኔ ጥፋቴ የአባወራነቱን ድርሻ ለእሱ አለመተዉ መቻሌ አለች ☺

የብዙዎቻችን ጥፋት ይመስለኛል 😞

ኒካህ አስሮ ሲወስደኝ ቤት ያገኘሁት ሀልጋ እና አንድ ብረድስት መክተፊያ 😃 ነዉ አለች ። በጥቅሉ ላገባ ነዉ ብሎ አላሰበበትም ነበር 😃

ከዛ በታጋባን በቀናቶች ዉስጥ እስከመቸ ገዝተን ---ገበያ ልሂድና የሚያስፈልገኝን ልግዛ ገንዘብ ስጠኝ ስለዉ 500 ☺ የማይሞላ ሰጠኝ አለች 😃

ልናገር ፈለኩና ---ገና ከአሁኑ ይበለኝ እንደ ብዬ የሰጠኝን ዝም ብዬ ተቀበልኩ እና ወደ ባንክ አመራሁ ።

ካለኝ ላይ የሚያፈልገኝን አንስቸ ገበያ ወጣሁ እና የቤት እቃ፣ አስቤዛ ፣ ለሳሎኑ ምንጣፍና ፍራሽ ከነ ትራሱ -----አሟላሁ ።

ከዛ በየ ሳምንቱ ገበያ ሲመጣ የአስቤዛ ስጠኝ ስለዉ የለኝም ይለኛል አለች 😊

እኔ አለኝ አይደል ---አልጨቃጨቅም በራሴ ማድረግ እየቻልኩ ብዬ ከራሴ ወስጀ አደርጋለሁ ።

የወንዱንም የሴቱንም ድርሻ ወስጀ ቀናቶች~~ ወራቶች አለፉና አመት ሆነን ።

የኔ አለቀ ።

አሁን አምጣ ማለት ጀመርኩ አለች ☺ ከዛ እሱ ባህሪሽ ተቀየረ ፣ ተጨቃጫቂ ሆንሽ ---- የማይለኝ የለም አለች ።

በስተመጨረሻ ተለያዩ ።

እህቴ ሞልቶ ቢተርፍሽ የባልነት ድርሻዉን ለእሱ ታይለት ።

አንዳንደዬ በፍቃድሽ አንችም እገዢዉ ያኔ ፍቅራችሁ ይጨምራል ።

እሱም ሀላፊነቱን ይወጣል።

የእሱን ሀላፊነት እየተወጣሽ በየት በኩል ትዝ ይለዋል 😃 በሰዉ ሀላፊነት አትግቢ 😊 ወላሂ የምሬ ነዉ ግን ማድረግ ስለምንችል ብቻ ራሳችንንም ትዳራችንንም አደጋ ላይ መጣል አግባብ አይደለም።

የባልነቱን ድርሻ እሱ መዉሰድ አለበት ። አይ እኔ እወጣለሁ ካልሽ ግን መጨረሻዉ አያምርም ☺

እናም መተጋገዙ መልካም ነዉ ካለሽ።

ግን ግደታሽንና ሀላፊነትሽን እወቂ!

የእሷም የኔም ምክር ነዉ 💝

Send as a message
Share on my page
Share in the group