Translation is not possible.

እኔ ማነኝ?

ባጎረስኩ እጄን ተነበስኩ

ባስጠልል ጎጆ ተነጠኩ

ብወልድም ልጆቼን ተቀማሁ

ውሃም እያለኝ ውሃን ተነሳሁ

ሰላም እንደናፈኩ ሰላሜን አጥቼ

ኢማኔንን ይዣለሁ አጥንቴን አጥቼ

ዱንያ ባያምርብኝ አኺራ እንዳላጣ

ከሰው ብገለልም ከእርሱ እንዳልወጣ

ገብቶኛልና የፈለጉትን ከእኔ

ነክሼ ይዣለሁ መዋደቁን ለዲኔ

በዚህም ፅናቴ ማየትን ይዟለሁ ሰው ያልገመተውን

ማሳየትም ያዝኩኝ ጥላት ያላሰበውን ሰውም ያላየውን

ግማሹ በዳይ ነው ሌላው ተባባሪ

ግማሹ ዝም ባይ ለሆዱ አዳሪ

እኔ በዚህ መሀል ሁሉን ብነጠቅም

ጀግኖች አፍርቻለሁ ጥላቴም አይስቅም

እኮ እኔ ማነኝ? ስሜን ካወቃችሁ

ከጎኔ ባትቆሙም ጥላትን ፈርታችሁ

ግን አውቃችሁኛል ፊዳ በመሆኔ

ለሰው ዘር ነፃነት በእልህ በኦኔ

ህዝቦቼን ሳስታጥቅ አፈሩን ፈልፍሌ

ልጆቼን ስቀልብ ቀልቤን አጠንክሬ

ሰውን አሰተማርኩት የነፃነትን ዋጋ

የሀገርን ፍቅር ጥላትን ሲዋጋ

እንዴት እንደሆነ መሄድ እየሳቁ

ሞት በማይሉትን ሞት ላይ ተሻግረው ሲዘልቁ

ህይወት እንደሆነ ለድል መታጨቱ

የሰው ዘርን ጥላት ሀይባውን ማጣቱ

ከልብ መውጣቱ እኔ በመግባቴ

የሰውን ቀልብ ሁሉ ሳደርገው ማጀቴ

ቀጣይ መሬቱን ነው አትጠርጥር ወዳጄ

መቼም አውቀኸኛል ስዋደቅ በደጄ።

እኔ ማነኝ?

ባጎረስኩ እጄን ተነበስኩ

ባስጠልል ጎጆ ተነጠኩ

ብወልድም ልጆቼን ተቀማሁ

ውሃም እያለኝ ውሃን ተነሳሁ

ሰላም እንደናፈኩ ሰላሜን አጥቼ

ኢማኔንን ይዣለሁ አጥንቴን አጥቼ

ዱንያ ባያምርብኝ አኺራ እንዳላጣ

ከሰው ብገለልም ከእርሱ እንዳልወጣ

ገብቶኛልና የፈለጉትን ከእኔ

ነክሼ ይዣለሁ መዋደቁን ለዲኔ

በዚህም ፅናቴ ማየትን ይዟለሁ ሰው ያልገመተውን

ማሳየትም ያዝኩኝ ጥላት ያላሰበውን ሰውም ያላየውን

ግማሹ በዳይ ነው ሌላው ተባባሪ

ግማሹ ዝም ባይ ለሆዱ አዳሪ

እኔ በዚህ መሀል ሁሉን ብነጠቅም

ጀግኖች አፍርቻለሁ ጥላቴም አይስቅም

እኮ እኔ ማነኝ? ስሜን ካወቃችሁ

ከጎኔ ባትቆሙም ጥላትን ፈርታችሁ

ግን አውቃችሁኛል ፊዳ በመሆኔ

ለሰው ዘር ነፃነት በእልህ በኦኔ

ህዝቦቼን ሳስታጥቅ አፈሩን ፈልፍሌ

ልጆቼን ስቀልብ ቀልቤን አጠንክሬ

ሰውን አሰተማርኩት የነፃነትን ዋጋ

የሀገርን ፍቅር ጥላትን ሲዋጋ

እንዴት እንደሆነ መሄድ እየሳቁ

ሞት በማይሉትን ሞት ላይ ተሻግረው ሲዘልቁ

ህይወት እንደሆነ ለድል መታጨቱ

የሰው ዘርን ጥላት ሀይባውን ማጣቱ

ከልብ መውጣቱ እኔ በመግባቴ

የሰውን ቀልብ ሁሉ ሳደርገው ማጀቴ

ቀጣይ መሬቱን ነው አትጠርጥር ወዳጄ

መቼም አውቀኸኛል ስዋደቅ በደጄ።

https://t.me/c/2003886752/235

ኢብኑ ነጃሽ

https://t.me/+fdLg-s0w2w83ODlk

Send as a message
Share on my page
Share in the group