ባሏ ከባሌ ይበልጣል ፣

ሚስቱ ከሚስቴ ትሻላለች፣

ቤታቸው ቤታችንን ያስንቃል ፣

ልጆቻቸው አቤት ማማራቸው!!

ቅናትና ምቀኝነት ከአላህ ጋር አደብ ማጣት ነው።

የሠጣችሁን ነገር ዉደዱ፣

ክፍፍሉን አመስግናችሁ ተቀበሉ፣

የናንተን ነገር በደንብ ያዙ፣

ዐይናችሁን አላህ ለሰዎች ከሠጠው ፀጋ ስበሩ፣

ስለተሠጣችሁ ብዙ ነገር እዩ፣

ያላችሁን ሌሎች ካላቸው ጋር እያነፃፃራችሁ አሳንሳችሁ አትመልከቱ፣

ለሁሉም አላህ ነው የሠጠው ፣

እሱም በጥበቡ ነው የሠጠው ፣

በፍትሁ ነወ ያከፋፈለው፣

በሰው ነገር ላይ ዐይናችሁ በሰፋ ቁጥር

ደረታችሁ ይጠባል

ደማችሁ ከፍ ይላል ።

ኑሯችሁ ቢጠብም ቢሰፋም አልሐምዱ ሊላህ በሉ።

አላህን በማመስገን ጤናችሁን ጠብቁ ::

https://t.me/MuhammedSeidAbx

Telegram: Contact @MuhammedSeidAbx

Telegram: Contact @MuhammedSeidAbx

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ
Send as a message
Share on my page
Share in the group