Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

# እውን ፈጣሪ አለን. ???

አንድ የእምነት ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር

አስተካካይ ቤት ይሄዳል። እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል።

ጸጉር አስተካካይ፦ታውቃለህ ፈጣሪ የለም ?

ተስተካካይ፦በመገረም እንዴት?

አስተካካይ፦አይታይህም?

ተስተካካይ፦ምኑ?

አስተካካይ፦እንዴ ፈጣሪ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ

ጦርነት፣ረሀብ፣ችግር፣ስርአት አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ

ፈጣሪ አንዴ ፈጥሮን ትቶን ሄዷል ወይ ሞቷል።

ተስተካካይ፦ታውቃለህ ጸጉር አስተካካይም የሚባል የለም

አስተካካይ፦ግራ በመጋባት እንዲህም በመገርም እንዴት?

ተስተካካይ፦ጸጉር አስተካካይ ቢኖርማ ጸጉሩ የጎፈረ ጺሙ

የተንዠረገገ ሰው አይኖርም ነበር።

አስተካካይ፦እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ጸጉር አስተካካይ

አለመምጣታቸው ነው እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ጸጉሩ

የተንዠረገገ እና የተንጨባረረ ጸጉር አታይም ነበር።

ተስተካካይ፦ትክክል ብለሀል በአለማችን ያለው ችግርም ይኸው

ነው ሰው ከፈጣሪው ስለራቀ ነው እንጂ ፈጣሪ ስለሌለ

አይደለም።

ከተመቸወ. ሼር

profileን ፣፣፣ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ follow me

ይህንንፔጅ Like Share Invite

በማድረግ የበኩሎን ይወጡ ።

Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас