Translation is not possible.

አስተማሪዎች የማስተማርን ክብደት ይወቁ❗

🚫"ያገኘኸውና የመሰለህን

ሁሉ ዝም ብለህ አትናገር!"

📂አል-ቀዕነቢይ እንዲህ ይላሉ፥["ኢማሙ ማለክ ወዳሉበት ስገባ እያለቀሱ ደረስኩኝ ምነው? ስላቸውም "ከእኔ ይልቅ ማልቀስ የሚገባው ማን አለ?! የምናገረው እየተጻፈ በየአቅጣጫው እየተሰራጨ ነው" ]አሉኝ።

⭕እንግዲህ ኢማሙ ማሊክን ያስለቀሳቸው ዒልማቸው በስፋት መተላለፉ ነው በዚህ ዒልምና ደረጃቸው ዕውቀቴ ተሰራጨ ብለው ሰግተው ይህን ያክል ከተጨነቁ የሳቸውን ዕውቀት ሩቡን እንኳ ያልደረሱ ሰዎች እርግጠኛ ባልሆኑበትና አላህ ዘንድ የሚሰጡት መልስ በሌላቸው ነገሮች ላይ ሰውን የሚያሳስቱና እንደልባቸው የሚናገሩ ሰዎችን ምን እንበላቸው?

🔹ኢማሙ ማሊክ በዚህ ብቻም አላበቁም የሐጅ ወቅት ሲደርስ ማስተማር ያቆሙ ነበር! "ምነው?" ሲባሉም፡-

( "ለሐጅ ከተለያየና ሩቅ ከሆነ ቦታ የመጡ ሰዎች ዛሬ የተናገርኩትን ሰምተው ቢሄዱና ከዛም ስህተት መሆኑን አውቄ ሀሳቤን ብቀይር እነሱን የት አግኝቼ ልነግራቸው ነው?!") ብለው መልስ ሰጡ!!

👉🏻ይህ ነው እንግዲህ የአላህ ፍራቻ ማለት!

እኛስ በምናስተላልፈው ነገር ምን ያክል አላህን እየፈራን ነው !!??

🔎ምንጩ ያልታወቀን ትምህርት የምናስተላልፍ ማስረጃውን ጠንቅቀን የማናውቀውን ንግግር የምንነጋገርና የምናሰራጭ ሰዎች ለራሳችን እንዘን!

🌐ሶሻል ሚዲያ ላይ ዝም ብለው ደስ ያላቸውን ሁሉ የሚለጥፉ ሰዎችም ከታላቁ ኢማም ይማሩ ምንም ነገር ከመልቀቃቸው በፊት ቆም ብለው ያስቡ ደሊሉን (መረጃውንም) ያገናዝቡ!

✍UAA

ሀሙስ 20/2/1439 ዓ.ሂ

@ዛዱልመዓድ

🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸

Send as a message
Share on my page
Share in the group