Translation is not possible.

ህፃናትና ስልክ‼

============

✍ አንዳንድ ወላጆች ገና ጥቅምና ጉዳትን፣ ሐላልና ሐራምን ላልለዩ ለጋ ህፃናት ይጫዎቱበት ዘንድ ስልካቸውን ይሰጣሉ። ያውም ኢንተርኔት ከፍተው፣ ያውም ቲክቶክና መሰል ሚዲያዎች ላይ ቪድዮዎችን እንዲያዩ!

ይህ ተገቢ አይደለም። ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ልጆች እናንተ ተመልከቱ ብላችሁ የከፈታችሁላቸውን ብቻ ሳይሆን ሌላም ነገር መጎርጎራቸው አይቀርም።

«ይሄ አያውቁም፣ ወደ ሌላ አይገቡም!…» የሚለውን ሽንገላችሁን ተውት። የዛሬ ልጆች ሳታስቡት ቀድመዋችሁ ሄደዋል። ት/ቤት አድርሳችኋቸው መጣችሁ እንጂ ጓደኞቻቸው እነማን እንደሆኑና ማን ጋር እንደሚውሉ አታውቁም።

ስልክ አትስጧቸው። በሐላሉ ዘና እንዲሉ ብላችሁ መስጠታችሁ አስፈላጊ መስሎ በታያችሁ ጊዜ ደግሞ ገደብ፣ ህግና ደንብ አብጁላቸው። ወይ በእናንተው ቁጥጥር ሆነው ወይም በሆነ ዘዴ ይመልከቱ።

አለበለዚያ ገና ከለጋነታቸው እናንተው ራሳችሁ በራሳችሁ ገንዘብ አበላሽታችኋቸው፤ ኋላ ሲጎለምሱ ልመልሳቸው ብትሉ እንኳ ከአቅማችሁ በላይ በሚሆንበት ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።

ትልቅ ኃላፊነት አለባችሁ። በዚህ እድሚያቸው ቂርኣታቸውን መቅራት፣ ትምህርታቸውን ማጎበዝና በሌሎች በሚጠቅሟቸው ነገሮች እንዲጫዎቱ ማድረግ እንጂ ጧት ማታ የስልክ ሱሰኛ እንዲሆኑ ማድረግ የለባችሁም።

ውዱ ነቢይ ይህን ብለዋል፦

( كلُّكم راعٍ وكلُّكم مسؤولٌ عن رعيتِهِ…

والرجلُ راعٍ على أهلِ بيتِهِ…)

«ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ። ሁላችሁም ስለምትጠብቁት ነገር ትጠየቃላችሁ። … ወንድ (ባል) በቤተሰቡ ጉዳይ ጠባቂ ነው።»

[አል-ቡኻሪይ: 2554፥ 2409፣ ሙስሊም: 1829፣ አቡ ዳውድ: 2928፣ አ-ት'ቲርሚዚይ: 1705፣ አ-ን'ነሳኢይ: 9173፣ አሕመድ: 5167]

√ ሳይንሱ የሚለውንም ልጨምርላችሁ። አንድ ከ13–17 እድሜ ባላቸው ታዳጊዎች ላይ የተደረገ የ Pew Research Centre ሰርቬይ እንደሚጠቁመው ከሆነ፤ 44% ታዳጊዎች ከእንቅልፋቸው ወዲያው እንደነቁ ስልካቸውን ያያሉ።

ስልክ ማብዛታቸው ከሚያስከትልባቸው የጤና ችግሮች መካከል፤ የአንገትና የወገብ (ስፓይናል ኮርድ) ህመም፣ Teen Tendonitis (TTT)፣ የስልክ ሱሰኛ ስለሚሆኑ ያለ ስልክ ሲሆኑ ከፍተኛ የድብርት ስሜት ውስጥ መግባት፣ መጨናነቅ/ ስጋት (Anxiety) ፣ ውፍረት፣ ለካንሰር በሽታም ይዳርጋል የሚል አለ። ማለትም ለ acoustic neuroma ይዳርጋል። በርግጥ እስካሁን ኮንፊርም ባይደረግም ከስልኮች የሚመነጨው ጨረር (radiation) ከስልኩ ጋር የተነካካውን የሰውነታችን ክፍል (በተለይም እጅ፣ በተለይም ኢንተርኔት ሲከፈትና እጅ ላይ ስልኩ ሲሞቅ) DNAን የመጉዳት አቅም ሊኖረው ይችላል።

ሌላው ከባዱ ችግር የእይታ (የዓይን) ችግር ይፈጥራል። በተለይም ህፃናት ለጊዜው ተፅዕኖው ጎልቶ ባይታይባቸውም እድሚያቸው ሲጨምር ገና በጊዜ ዓይነ ስውር እንዳታደርጓቸው። የcell phone vision ምልክቶቹ stress, redness, burning sensation, blurred vision, and dry eyes ናቸው።

ተጨማሪ ፔፐሮችንና ጆርናሎችን ከፈለጋችሁ እነዚህን አንብቡ።

1) Cell Phones and Cancer Risk; National Cancer Institute

2) Aswitha Priya Sadagopan, et al.; Prevalence of Smartphone Users at Risk for Developing Cell Phone Vision Syndrome among College Students; Journal of Psychology & Psychotherapy (2017).

3) Sehar Shoukat; Cell phone addiction and psychological and physiological health in adolescents; EXCLI Journal (2019).

4) Amanda Lenhart, et al.; Teens and Mobile Phones; Pew Research Center (2010).

በአጭሩ ተጠንቀቁ። የጠቀማችኋቸው መስሏችሁ እንዳትጎዷቸው። ጭራሽ አንዳንዱ ወላጅማ ለራሳቸውም ስልክ ገዝቶ የሚሰጥ አለ። ልጁም «የኔ ጓደኞች ስልክ ይዘው እኔ ብቻ…» እያለ ያለቃቅሳል። ወላጅም የኔ ልጅ ከማን ያንሳል ብሎ ይገዛል። ተወው! አሁን ያልቅስ! ኋላ ዓይኑን አጥቶ ከሚያለቅስ! አሁን የጎዳኸው መስሎት ቢጠላህም ኋላ ሲገባህ ይወድሃል። በትህትና ለነርሱ ጥቅም ብላችሁ እንደሆነ የምትከለክሏቸው አብራሩላቸው። ግን እንዳልኳችሁ ከቴክ ነክ ነገር የራቁ በደዊይ እንዳይሆኑም ለትምህርት በሚሆን መልኩ በእናንተ ክትትል አሳዯቸው።

አላህ ያግዘን! ያግዛችሁ! በዲኑም በትምህርቱም ጠንካራ ልጅ እናፍራ።

||

ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ

=========

ኖቬምበር 28, 2023 G.C.

||

t.me/MuradTadesse

https://ummalife.com/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group