☑️ ዒልም የማይጠገብ ስብእና..!!

~ ኢብኑ ተይሚያ

አምሮታቸው ፣ጉጉታቸው ፣ኢልም መቅስም ፣ ኢልም ማስራጨት ነበር። ለኢልም ሲሉ የለበሱት ልብስ ከላያቸው ላይ ከሚያድፍ ትተውታል። ለዒልም ሲሉ ከፍተኛ ስልጣንን አሽቀንጥረው ጥለዋል። ኢብኑ ተይሚያ ባሉበት የሆድና የሴት ጉዳይ አይነሳም። አጥጋቢ ድምዳሜ ላይ ያልደረሱበትን ጉዳይ ከጫፍ ሳይደርሱ ልባቸው አያርፍም። አንዳንዴ አንዲትን የቁረአን አንቀጽ እያጠናሁ ምናልባትም ወደ መቶ አካባቢ ተፍሲሮችን የማገላብጥበት ጊዜ አለኝ" ይላሉ።

{ አልዑቁድ : 42}

Send as a message
Share on my page
Share in the group