Translation is not possible.

በቁጥጥራቸው ስር ከነበረችው እስረኛ ለቀሳም ጄኔራሎች የተፃፈ ደብዳቤ

ጌታዬ ሆይ!

ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ

"ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ። በእርግጥም ነገ እንደምንለያይ አውቅ ነበር። ለልጄ ኤሚሊያ ያሳያችኋት ሰብዓዊነት፣ እንደፈለገች ስትንቀሳቀስ ወደ ክፍላችሁ እንደልቧ ዘልቃ ስትገባ በፈገግታ እየጋበዛችሁ ስትቀበሏት በእርግጥም እንደ ወላጆቿ ነበራችሁ።

ጓደኞች ብቻም ሳትሆኑ እውነተኞች ወታደሮች ብቻም አይደላችሁም ጥሩ አፍቃሪዎች እንጂ። ደግሜ ደጋግሜ አመሰግናችኋለው። ስላሳለፍናቸው ብዙ ሰዓታት እንደ ሞግዚት ሆናችሁ ስለተንከባከባችኋት አመሰግናለሁ። ትዕግስትን ተላብሳችሁ ከጣፋጩ እየሰጣችሁ ከፍራፍሬም መግባችኋታል።

ልጆች በግዞት ውስጥ መሆን የለባቸውም። ግና እንደናንተ ዓይነቶች በመንገዳችን ገጥመውን ጥሩ ሰዎችን አስተዋውቆናል። ሴት ልጄ በጋዛ ንግስት ነበረች። የምታብረቀርቅ ሉል። የምታበራ አልማዝ።

በረጅሙ ጉዟችን ከተወለድን እስከ አሁን ከተራ ወታደሮች እስከ አመራሮች በርኅራኄና በፍቅር ጠላቶቻቸውን የሚንከባከቡ አንድም አላገኘንም። ለዘላለም የምስጋናችሁ እስረኛ ሆኛለሁ። ሁሌም ስለናንተ መልካምነት እናገራለሁ።

እናንተ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆናችሁ፣ ከባድ ችግርን እያስተናገዳችሁ፣ ቤተሰብ ዘመዶቻችሁን በሞት እያጣችሁ ለእኛ ግን ጥሩ ነበራችሁ። ይህቺ ዓለም ፈቅዳ ዕጣ ፈንታችን ገጥሞ ዳግም እውነተኛና መልካም ጓደኛሞች እንድንሆን እመኛለሁ።

ከነቤተሰቦቻሁ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። ለሁላችሁም መልካሙን ሁሉ ከጤና ጋር እመኝላችኋለው" ከዳኒያልና ከኤሚሊያ

© Mahi Mahisho

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group