Translation is not possible.

ሶስት ፍልስጤማውያን ተማሪዎች በአሜሪካ ካምፓስ አካባቢ ተተኮሰባቸው

በአሜሪካ ቬርሞንት ቅዳሜ እለት ሶስት የፍልስጤም ተማሪዎች  የጥይት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሲሆን የጥላቻ ወንጀል ስለመሆኑ ፖሊስ እንዲያጣራ የተጎጂ ቤተሰቦች አሳስበዋል። ሂሻም አዋርታኒ፣ ታህሲን አህመድ እና ኪናን አብዳልሃሚድ በቨርሞንት ካምፓስ አቅራቢያ ከአንድ ሰው ጋር ፀብ ውስጥ ከገቡ በኃላ በጥይት መመታተቸውን የበርሊንግተን ፖሊስ ተናግሯል። የፖሊስ መኮንኖቹ ምክንያቱን በማጣራት ላይ ሲሆን ጥቃት ሲደርስባቸው ኬፊዬ የተሰኘውን ባህላዊ ስካርፍ ለብሰው እና አረብኛ እየተናገሩ ነበር ብለዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን በማፈላለግ ላይ ይገኛል። የበርሊንግተን ፖሊስ አዛዥ ጆን ሙራ ሁለቱ ተጎጂዎች በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን በመግለፅ ሦስተኛው በጣም የከፋ ጉዳት ደርሶበታል ሲሉ ተናግረዋል።ሦስቱም ተጎጂዎች በራማላህ ትምህርት ቤት ተምረዋል፣ የቤተሰብ አባላት እንደተናገሩት ደግሞ አብዳልሃሚድ፣ በሃቨርፎርድ ኮሌጅ መማሩን ገልፀዋል። የተቀሩት ሁለቱ በብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትሪኒቲ ኮሌጅ ገብተው ሲማሩ ነበር። ከተጎጂዎቹ የአንዱ አጎት የሆኑት ሪች ፕራይስ፣ ሦስቱ በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እና የስምንት ዓመት ልጅ የልደት ድግስ ላይ ከጥቃቱ በፊት ተገኝተው ነበር ብለዋል።

ከቤታችን ከወጡ ከአምስት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአምቡላንስ የሳይረን ድምፅ መሰማቱን የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል።ይህንን ጥቃት እንደ ጥላቻ ወንጀል መቁጠርን ጨምሮ የህግ አስከባሪ አካላት ጥልቅ ምርመራ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን ሲሉ አክለዋል። አጥቂው ግለሰብ ለፍርድ እስካልቀረበ ድረስ ምቾት አይኖረንም ሲሉ ተደምጠዋል። የአሜሪካ እስላሚክ ግንኙነት ምክር ቤት ተጠርጣሪው ማን እንደሆነ መረጃ ለሚሰጠን የ10,000 ሺ ዶላር ጉርሻ እሰጣለሁ ሲል አስታውቋል።

የቬርሞንት ሴናተር እና የቀድሞ የዴሞክራት ፕሬዚዳንታዊ እጩ በርኒ ሳንደርስ ጥቃቱን አውግዘዋል። ሳንደር በኤክስ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት  “ሦስት ወጣት ፍልስጤማውያን እዚህ ቡርሊንግተን ቨርሞንት ውስጥ በጥይት መመታቸው አስደንጋጭ እና እጅግ አሳዛኝ ነው። ጥላቻ እዚህም ሆነ በየትኛውም ስፍራ ቦታ  የለውም” ብለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም የፍልስጤም ሚሲዮን ኃላፊ አምባሳደር ሁሳም ዞምሎት የሶስቱን ወጣቶች ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በማጋራት “በፍልስጤማውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው የጥላቻ ወንጀሎች መቆም አለባቸው” ሲሉም አክለዋል።

umma life news

-seya_smoke

don't forget #follow and #like

Send as a message
Share on my page
Share in the group