#ቁርአንን #መሕር #ማድረግ #ይቻላል?
~~~~~~~~~~~~
ጥያቄውን በቀጥታ ከመመለሳችን በፊት መሕር ምንድን ነው?የሚለውን እንመልከት መሕር ማለት ልክ እንደ ወልይ፣ ሻሂድ ፣ለፍዞል ዓቅድ ለኒካህ ሩክን(መሠረት) ነው።መሕር ለማነሱም ለብዛቱም የተቀመጠ ልኬት የለውም ሁለቱ ተጋቢዎች የተስማሙበት መጠን ሁሉ ይቻላል። ከመፋቂያ ፣ ቀለበት እስከ Mullins
ይቻላል። ግን ኸይሩ የተሻለው ቀለል ያለው መሕር ነው።የመልእክተኛው
صلي الله عليه وسلم
ሁሉም ሚስቶች ልጆቻቸው ሳይቀሩ ቀለል ባለ መሕር እንደተዳሩ ታሪክ ያስረዳል።ያላገባ ወጣትንም ወደ ትዳር ለመገፋፋት የመሕር መቅለል አስተዋፅኦ አለው።
ወደ አነሳነው ጥያቄ ስንመለስ ቁርአንን መሕር ማድረግ በሁለት ልንከፍለው እንችላለን።
1/ቁርአንን ለሚስቱ ማስተማር
2/ቁርአኑን (text book)ን ወይም ኮፒ ቅጅውን መስጠት በሚል ሁለቱንም በዝርዝር እንመልከት በቁጥር 1/በተጠቀሰው አረዳድመሠረት ቁርአንን መሕር ማድረግ ይቻላል።ነብዩ
عليه الصلاة والسلام
ለአንድ ተከታያቸው ለመሕር የሚሰጠው ቁሳዊ ነገር በማጣቱ በቃ ከሐፈዝከው ቁርአን አስተምራት ብለው እንደዳሩት ተረጋግጧል።ነገር ግን መጀመሪያ ገንዘብ መቀደም አለበት ገንዘብ እያለ ሳይጠፋ ዘሎ ቁርአን አቀራታለሁ ማለት {ከፈረሱ ጋሪው }እንደሚባለው ነው። ቁርአንን፣ ዲንን ለሴቶች ማስተማር ሲጀመር የባል ግዴታ ነው።
በቁጥር 2/ በተጠቀሰው አረዳድ ከሆነ ዑለማኦች ልዩነት አላቸው የሻፊዕይ፣ ሐነፍይ ፣ማሊክይ ሊቃውንቶች ቁርአንን መሸጥ መለወጥ ይቻላል ስለሚሉ ለመሕር ቁርአኑን ቢሰጥ ችግር የለውም ብለዋል።የሐናቢላ ዑላማኦች ግን ቁርአንን (text book)ን መሸጥ፣ መለወጥ አይቻልም ይላሉ።መሕር ማድረጉም ቢሆን በከንዘብ ምትክ ስለተተካ ቁርአንን እንደመሸጥ ነውና ክልክል ነው ይላሉ። ስለዚህ ገንዘብ መስጠት የሚችል የትኛውም ባል መሕሩ ገንዘብ ሁኖ ቁርአኑን ቢያስተምር በስጦታም ቢያበረክትላት የተሻለ ነው ። አሏህ ከሁሉ አዋቂ ነው
✍ ሙሐመድመኪን ሁሴን