Translation is not possible.

የቀሳም ብርጌዶች መደራደርያ ይህ የፍልስጤሞች ቁልፍ ሰው ማንነው?!

እርሱ ማስተር ማይንዳችን ነው ይሉታል። የእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ ባለጥላው መሪ በማለት ይጠራዋል። የወራሪዋን ጦር ቁም ስቅል ያሳየ፣ የሞሳድ ኤጀንቶችን ያደናገረ ጀግና የጦር መሪ እንደነበር ራሳቸው በአንደበታቸው ይመሰክሩለታል። ሰውየው በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ከደቡብ ኮሪያ በማእረግ ተመርቋል። በጁዶ ካራቴ ከፍተኛ ማዕረግ አለው። ተቀጣጣይ ፈንጅዎችን መስራት ለሱ ምግብ እንደማብሰል ቀላል በኮምፒውተር ሰበራ/ሃኪንግም ኤክስፐርት ነው።

ከዛሬ 21 አመታት በፊት ነበር በጠ/ሚ ናታንያሁና በእስራኤል ቱባ ባለስልጣናት ከSituation room በተመራ ሚሽን በቁጥጥር ስር የዋለው።

መያዙን ሲሰሙ በደስታ ፈነደቁ። ውስኪያቸውን እየተራጩ አደሩ። ናታንያሁ በዛው ለሊት ለሚስታቸው ቀጥታ ደውለው እንዲህ ማለታቸውን ጋዜጦች ከተቡ

"አስቸጋሪውና የሙጃሂዶቹን ማስተር ማይንድ፣

ባለ ጥላውን መሪ ያዝነው!.. አዎ በትክክል ይዘነዋል!.. ራሱ ነው"

የተፈረደብት (5200) አመታት ነው።

ሰውየው ዐብደላህ አልበርጉሲ ይሰኛል።

ይለቁት ይሆን የምናየው ይሆናል። ባለበት አላህ ይጠብቀው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group