Translation is not possible.

የፍልስጢኖችን ሀገር የመመስረት መብት ያጣጣለው የኔዘርላንድ ፓርላማ አባል ንግግር ተወገዘ!

የፍልስጢን ህዝቦችን ከትውልድ ቀያቸው ለማፈናቀል ፅንፈኛው የኔዘርላንድ ተወካይ ያቀረበውን ጥሪ የዮርዳኖስ(ጆርጃን)እና ፍልስጢን ውጭጉዳይ ሚኒስትሮች አውግዘዋል።

የዮርዳኖስ ውጭጉዳይ ሚኒስተር ፅንፈኛ የሆላንድ ፓርላማ አባል የሆነውን #የዊልደርስን አስተያየት “ዘረኝነት” ነው በማለት አውግዟል።

የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የፍልስጤማውያንን መንግስት የመመስረት መብት በመንፈግ ወደ ዮርዳኖስ እንዲፈናቀሉ የጠየቀውን የኔዘርላንድ ፓርላማ አባል #ገርት_ዊልደርስ የሰጠውን ፍርደገምድል ቆሻሻ አስተያየት “የዘረኝነት መግለጫዎች” በማለት አውግዘዋል።

የሆላንድ ፓርላማ አባልን መግለጫዎች "በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና በደል የሚደግፍና በእጣ ፈንታቸው ላይ ግልጽ የሆነ ጣልቃ ገብነትን ለማባባስ የቀረበ ጥሪ ተመልክተናል”ካለ በኋላ “የኔዘርላንድ ፓርላማ አባል የፍልስጤም ህዝብን መብት የነፈገበትን የዘረኝነት ንግግር አጥብቀን እናወግዛለን፣በገዛ ሀገራቸው ምሥራቃዊ እየሩሳሌም ዋና ከተማነት የነጻነት ግዛታቸውን የመመስረት መብታቸውን የነፈገ፣ህዝባችን እንዲፈናቀል፣ችግራቸውን እንዳይፈታ እና  ወደዮርዳኖስ እንድሰደዱ በተናገረው የብልግና አስተያት የኔዘርላንድ መንግስት እነዚህን መግለጫዎች በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት እንዲያወግዝ እና ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቋል።

ጽንፈኛ የሆላንድ ፓርላማ አባል ገርት ዊልደርስ ንግግር በተመለከተ የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #አይመን_ሳፋዲ ለሆላንዱ አቻቸው #ሃንኬ_ብሮንስ ባደረጉት የስልክ ጥሪ አውግዘዋል።

የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ እንዳስታወቀው አልሳፋዲ በስልክ ጥሪው ወቅት በአክራሪው የፓርላማ አባል ገርት ዊልደርስ የተነገረውን የዘረኝነት አቋም ውድቅ በማድረግ የፍልስጤም ህዝብ ነፃነቱን የማግኘት እና በአገራዊ ብሄራዊነቱ ላይ ያለውን የማይገረሰስ መብት አረጋግጧል።

ሚኒስተሩ በዮርዳኖስ ወጪ የፍልስጤምን ጉዳይ መፍታት ይቻላል የሚለው “ቅዠት”መሆኑንም አስምረውበታል።በትላንትናው እለት በኔዘርላንድ በተካሄደው የህግ አውጭ ምርጫ በጌርት ዊልደርስ የሚመራው የቀኝ ፅንፈኛው ፀረ እስልምና እና ፀረ-ስደተኛ የነፃነት ፓርቲ አሸንፏል።

ለእስልምና ባለው ጥላቻ የሚታወቀው የቀኝ አክራሪው ዊልደርስ በቅርቡ የፍልስጤም ህዝብ መብትን በተለይም ነጻ የሆነች ሉዓላዊት ሀገር የማግኘት መብታቸውን እና የፍልስጤም ጉዳይ በዮርዳኖስ ኪሳራ የመፍታት ቅዤቱን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ምንጭ:RT

#????????????????????

https://t.me/Seyfel_Islam

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group