Translation is not possible.
بسم الله الرحمن الرحيم
        
              
              👉ግጥም👈
 
  
          👇ፍንትው ሲል👇
            👇ያ ም ራ ል👇
 
ለጌታችን الله ምስጋና ይገባው
አብራር ምንጭ ሆኖ የፊትና ዋናው
 
[ ] በወንድሞች መሀል ተከስቶ የነበረው
[ ] ነገራቶች ታውቀው ግልፅ ሆኖ ስናየው
 
[ ] ሁሉም የገባበት  ሲገልፅ ስላለፈው
[ ] ያ ሁላ ግርግር አለፈ በፊትናው
[ ] የሩቁም የቅርቡ ጉዳዩን እንደሰማው።
 
 
[ ] ወንድሞች ገለፁ  ወደ الله በተውበት
[ ] ከገቡበት ወጡ ከወንጀል ባሉበት
 
[ ]  ይቅርታን ጠየቁ ከተናገሩበት
[ ] ለሌችም ጭምር ትላንት ከበደሉት
 
[ ] እንዲህ ያስደስታል ኸይር ስራ መስራት
[ ] ነበር ከበፊትም ወንድሞች የመከሩበት
 
[ ] ዛሬ እውነታው ሲታው በጣም አማረበት
[ ] እንደዚህ አይነት ነው ተመካሪ ማለት
[ ]  ጀባሩ ወፍቆት ያለው ሚሰማበት።
 
 
[ ] አሁንም ነቃ በሉ ያልመለሳቹ
[ ] ተስፋ አትቁረጡ ከአዛኙ ጌታቹ
 
[ ] ማንንም አትፍሩ ለመውጣት ከወንጀላቹ
[ ] ብትጠሩ ይሻላል የاللهን ፊት ፈልጋቹ
 
[ ] አሸፈረኝ ከሆነ በኩራት ተይዛቹ
[ ] ማንንም አትጎዱም እዘኑ ለራሳቹ
[ ] በአሽራሪያ  ሸር  ለተነደፋቹ።
 
 
 
        👇  [x] የመንጠቆው ብዛት👇
 
ከቀኝ ከግራ ሀቅን ለማስለቀቅ
ሲያንዣብቡ ወንድም ለመፋረቅ
 
መሞቻቸው ደርሶ ካልሆነ ለመውደቅ
መስሎህ ከሆነማ አንድም የለም ንቅንቅ
 
ጊዜህን አትፍጅ    ሳይመሽብህ ፈትለክ
ከሸርህ الله ጠበቀን  በባዶ አትድረቅ።
 
 
[ ] በጣም ተገረምን በዘንድሮ ነገር
[ ] ምድረ አሸር ባሸሩ ጋጋታ ሲፈጥር
 
[ ] የጨቅላው ስብስብ የሚዲያው ግርግር
[ ] እንደው ይወራጫል አንድ የለው ቁም ነገር
 
[ ] አለ ማይቀመጥ ወይ ሀቅ ማይናገር
[ ] የባጢል ባንድራ እያውለበለበ ሚኖር
 
[ ] ሲያናውጠው ፊክራ ከዛ ማዶ መንደር
[ ] ከሚዘባርቅ ያለ እውቀት ከሚናገር
 
[ ] ያለ ቦታው ገብቶ ከሚለው ድንግርግር
[ ] እጅ ወደላይ ብሎ ዞር ቢል ይሻለው ነበር
[ ] እንደ ቂርጣስ አይነቱ ለቂጡ ግርግር።
 
 
[ ] ሌላውም ይገባል ተስብሮ ሊወጣ
[ ] ብዙ ጉድ አሳየን ወይ የዘንድሮ ጣጣ
 
[ ] መቆም ያቃተው የግብስብስ እጣ
[ ] በየ አቅጣጫው   ሰብስቦ አመጣ
 
[ ] የበሰበሰ ክምር   ምንም ላያመጣ
[ ] የተህሪሽ አይነት ሰብስቦ ቢያንጣጣ
 
[ ] ሀቅ እስካለተናገክ ምንም አታመጣ
[ ] ይልቁንስ ተመከር ሳታስነቃ ውጣ
 
[ ] ላንተ ይሻለሀል ነገር ከምታመጣ
[ ] መዘዙ ብዙ ነው  ከሀቅ የወጣ
[ ] ከማርስም ይሁን ከጅቡቲም መጣ።
 
 
[ ] ሌላውም ይገባል በቤ ፊያት መሳይ
[ ] እውቀት ሳይኖረው በባዶ አስመሳይ
[ ] ግርግሩ ሲታይ ከባጃጅ ተመሳሳይ።
 
 
[ ] በስሜት ተነስቶ በጀህሉ ሚቧርቅ
[ ] ስለ ጅህልና ያወራል አሊምን የማያውቅ
[ ] በባዶ ፈረስ ላይ  እንደው ሚመፃደቅ።
 
 
[ ] ወደ ላይ አድርጎ ተንጋሎ ሚተፋ
[ ] በውሸት ተሞልቶ  ደባው የከፋ
[ ] ያለ ቦታው ገብቶ በባዶ ሚነፋፋ።
 
 
[ ] ከአስተማሪዎቹ ቆይቶ በመማር
[ ] ምንም ሳይቀፈው ያገኘው ሚናገር
 
[ ] ዘላን እንደ ቁንጫ ሀያዕ የለው ክብር
[ ] ዛሬ ዳዒ መሳይ ተወጥሮ በሸር
 
[ ] ተሞርዶ ወጣ በፊክረተል አሽራር
[ ] ግባ ወደሜዳ አንተም እስክትሰበር።
 
 
[ ] እንደው መስሎህ እንጂ የታሉ አባቶችህ
[ ] እኛ  ጀግና      እያሉ  ካንተም የተሻሉህ
 
[ ] ተውበት እያደረጉ ወንድም ከአጠገብህ
[ ] አንተ በቤ ፊያት ማትነቃ ተኝተህ
 
[ ] ነገ ልትመለስ በወንጀል ተነክረህ
[ ] የአለቃው ትዛዝ ነው ግንባር ግባ አለህ
 
[ ] በል እዘንላት ቀስ ለጭንቅላትህ
[ ] በሱና ሪጃሎች ብለው ግንባርህ
 
[ ] ምንነትህ አጥተህ ዱቄት ከሚያደርጉህ
[ ] ወደሗላ ውጣ አያዋጣም ብለህ
 
[ ] ላንተ ከማዘን ነው ኤሄነው ሚሻልህ
[ ] ያ ሙሀመድ ሰይድ እዘን ለአናትህ።
 
 
 
[ ] الحمد لله
[ 📝] ከ አብዱሰላም ሙሀመድ
Send as a message
Share on my page
Share in the group