Translation is not possible.

بسم الله الرحمن الرحيم

👉🛑#ግጥም??

📕#አርእስት:-"#ተበጥሩቅ

#ያጠናው

#እስኪያልቅ\"

ሰዎች አላይ ብለው ማዶ ሲያንጋጥጡ

አልታይ ብሏቸው ጅቡቲ ሲያፈጡ

ቢንጠራራ አያይ ቢቆም በጥፍሮቹ

እኩያው እኮ ነው ተዉንጂ ሰዎቹ

ድምፁን ጮክ አድርጎ ሲሳደብላቹ

አሁን ትኩረት ስጡት ቆሟል በጣቶቹ

የፌስ ቡኩ ቲልሚዝ ባላአዲስ መንሀጁ

ያቅሙን ይፍጨርጨር እስኪያልቅ ነዳጁ

ሲበጠረቅ ይዋል ያጠናው እስኪያልቅ

ኢንተርኔት ተዘግቶ ይህ ኪታብህ ሳያልቅ

ደርስ እንዳይቌረጥ ቶሎ ትኬት ቁረጥ

ፈጠን ብለህ ብረር ባህሩ ላይ ሳትጠልቅ

#ቂለተል አደቡ አህላቅ አስተማሪ

ካፍህ የሚወጣው በጣም አሳፉሪ

#ኢስላማዊ አህላቅ በልዩ ቀማሪ

ማእድን ሊያወጣ በጥልቅ ቆፋሪ

#መንሀጅ በሀበሻ ሊያወጣ ታታሪ

መሬት ተደርምሳ ታጣለህ ቀባሪ

የሰው እጥረት አለ በል እስቲ እሹሩሩ

የሰው ልጆች ሁሉ ባንድ ተደመሩ

መንሀጅ አሊፍ ባታ ብላቹ ጀምሩ

# የነ ጀማል ደእዋ ጀርህና ተእዲሉ

አህላቅ ብልሹነት ከሆነ በምሩ

ያንተ እነሱን መስደብ እንዲህ መማረሩ

የአናት ቅቤ ነው ወይ የማር ክምሩ

#ያላቅም መሰቀል እንዲ እንደቀለለህ

መፈጥፈጥ መኖሩን ማንም አልነገረህ

ተንቦጣረርክ እኮ ሰው ላንተ አፈረ

ጠንቅቆ ሚያውቅህ ስትድህ የነበረ

ድመት ተቆጥታ አብጣ ተኮፍሳ

ድመት ያው ድመት ናት አትሆንም አንበሳ

ሚሳኤል ተኩሰው ደእዋዉን ድርመሳ

ዛሬ ጨቅላው መቶ ባላ ቢያነሳ

ወፊቷን እማይገል እንኳንስ አንበሳ

#የሀበሻ  ጀግኖች እነ ጀበሎቹ

ዉር ውር ለሚለው እንኳንስ ለምቹ

ተጔዥ ይቀጥላል ቢጮሁም ውሾቹ

ስህተት ስታጡ ስንት እንዳልጮሀቹ

ወገባቹ ሲዝል ቁፋሮ ደክሟቹ

ሰርች ብታደርጉ ኖ ሪዛልት ቢላቹ

ስራ የማይፈታው ድንቁ ፋብሪካቹ

ተስጂል አልነበረም ብሎ አረፈላቹ

     

الحمد لله

✍ተፃፈ ከእህታችን الله ይጠብቃት‼️

https://t.me/AlEmanhabssha

Telegram: Contact @AlEmanhabssha

Telegram: Contact @AlEmanhabssha

القناة الرسمية للدعوة السلفية في الحبشة {إياك والتحزب} {إن الذين فرقوا دينهم وكانوا شيعا لست منهم فى شئ} #ቁርአንና ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ እንረዳ በዚህ ቻናል:-የሱኒይ፣ ዑለማ ፈትዋዎች፣ዱሩሶች፣ሙሀደራዎች የሀበሻ ሰለፍይ ዱዐቶች ጥሪ የሚተላለፍበት ቻናል ነዉ‼ ዳዕዋ አሰ–ሰለፊያ
Send as a message
Share on my page
Share in the group