👉ስሚኝ እናት አለም.....!?
 
«ሰለፍያ»
---------------------
ልጅሽ እየለፋ ህግሽን ለማክሰል፡
አጭበርባሪ ሆኖ በዝቶበት ማስመሰል፡
ስሜት እየመራው ሳየው ሲብሰለሰል፡
እኔም በማውቅበት ደብዳቤ ፃፍኩልሽ፡
የልጆችሽ ነገር ሆኖኝ እንቆቅልሽ፡
----------------------------
ሰለፍያ.....
ምንም ነገር ብሆን ባምርም ብገረጣም፡
ኑሮ ቢቀያየር አገኝቼ ባጣም፡
በስኬት መሰላል ብወርድ ብወጣም፡
እናትነትሽን ልጅሽ ነኝ አላጣም፡
ሰለፍያ.....
ከትረካ በላይ በብዙ ብገፋም፡
ሀዘን ተሰምቶኝ ምን ያህል ብከፋም፡
ስሜት አሸንፎኝ ምን ብዙ ባጠፋም፡
ከእናቱ ቤት ደጃፍ ማንም'ኮ አይጠፋም፡
ሰለፍያ....
የስምሽ ጭልፊቶች በበዙበት ሀገር፡
ደፈርከኝ ሳትይኝ እውነቱን ብናገር፡
አዋቂ ነኝ ከሚል አስመሳይ ወንበዴ፡
የኔ ቢጤ ጃሒል ይሻላል አንዳንዴ፡
ኢዕራበይን ባልቀራ ባይገባኝ አልፍያ፡
ለኔም ግን እናት ነሽ ደዕዋ ሰለፍያ!?
-----------------------------
በኑረዲን አል-አረቢ➊❹❹❹
-----------------------------
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
----------------------------
Send as a message
Share on my page
Share in the group