Translation is not possible.

✍አጃኢብ   የሆነ  ገጠመኝ ✍

☞ሰውየው   ፈጅር  ሶላት  ለመስገድ  ከንቅልፉ ተነሳና ልብሱን ለባብሶ ውዱእ አድርጎ  ወደ መስጂድ ጉዞ ጀመረ ግማሽ መንገድ እንደደረሰ  አንዳለጠውና ወደቀ

ልብሱ ቆሸሸበት  ወደ ቤቱ ተመለሰና ልብሱን ቀይሮ ውዱእ ጀድዶ እንደገና ወደ መስጂድ ጉዞ ጀመረ

አሁንም  መሀከል መንገድ ላይ ሲደርስ  አዳለጠውና ወደቀ ልብሱም ተበለሻሸበት   እንደገና ወደ ቤቱ ሄደና ልብስ ቀይሮ  ውዱእ  አድሶ ለ 3 ተኛ ጊዜ ወደ መስጂድ መጓዝ ጀመረ   ቅድም  አወደቀበት ቦታ አንድ ሰው  መብራት በ እጁ ይዞ ጠበቀው

ከዛም  ማነህ ብሎ ጠየቀው አይ እኔ  እዚህ ቦታ ላይ  ሁለት ጊዜ ስትወድቅ አየሁህና መብራት ላብራልህ ብዬ ነው  አለውና  እያበራለት መስጂዱ በር ድረስ አደረሰው  ከዛም  በል  እንግባና እንስገድ ሲለው  አልገባም አለ ቢደጋግምበትም እንቢኝ አለው  

ለምን ነው  መስገድ የማትፈልገው ብሎ ሲጠይቀው እኔ  ሸይጧን ነኝ     እኔ ነኝ  ቅድም  ሁለት ግዜ እንድትወድቅ ያደረኩህ መጀመሪያ   ያስወደኩህ  ተመልሰህ  ቤትህ  እንድትሰግድ ፈልጌ ነበረ አንተ ግን  ተመልሰህ መጣህ  የዚህ ግዜ አላህ  ወንጀልህን ማረልህ ሁለተኛ  ሳስወድቅህና ወደ ቤትህ ስትመለስ ቤተሰቦችህን ማረልህ ለ ሶስተኛ  ጊዜ እንዳላስወድቅህ  የመንደሩን ሰው በሙሉ ይምራቸዋል ብዬ ፈራሁ  ብሎ  ነገረው።

ለሸይጧን በር አንክፈት

የሸይጧን ነገር  ይገርማል ሀሳቡ  ሁላችንንም ሰብስቦ ጀሀነም  ማስገባት ነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group