ዱንያ በእርግጥ ከባድ ነው። ግን ደግሞ የተሻለ ገንዘብ ለሰጠ ቤተ እምነት ሁሉም አይፈረምም። አንድ "ከፈርኩ" የሚል ወንጌላዊ "እስልምና ትክክል ነው" ብሎ ከአንዴም ሁለቴም ወንድሞች ጋ መጥቶ ሸሀዳ ይዟል። ወንጌላውያን ጋር የሚያገኘው ጥቅማጥቅም እዚህ አለመኖሩ ግን ነፍሲያውን ፈተነውና ለለመደው ጥቅም ሲል መልሶ "እናንተ ትሻሉኛላችሁ" ብሎ ከፈረ። እንዲህ አይነት ሰው የተሻለ ገንዘብ ሩቅ ምስራቆች ጋር ካገኘ ቡድሂስት ከመሆን አይመለስም። ከአመታት በፊት ተቸግሮ ዳዕዋ ያደርግ የነበረ ሰው የቤትና የመኪና ምቾት አታሎት የነሱ ሰባኪ ሁኖ ቴሌግራም ላይ ተወያይተን እንደነበር አስታውሳለሁ። በእርግጥ ሰውየውን አላውቀውም ነበር ኃላ ነው ከኡስታዝ አቡ ሐይደር ጋር ስናወራ ማንነቱን ያወቅኩት። ከንጽጽር ኡስታዞች አንዱ ግን ስለሁኔታው በአካል ሲጠይቀው የመለሰው መልስ ክርስቲያኖች ቢሰሙት እንዳታለላቸው ተረድተው ወዲያውኑ የሚሰጡትን ብር እንደሚያቋርጡበት አያጠራጥርም። እነዚህ አይነት ሰዎች በመጨረሻ ጊዜያቸው ሸሀዳ ብለው ጥፋታቸውን አክስመው አሏህን እንደሚገናኙ ተስፋ ያደርጋሉ። ሞት አማክሮ አይመጣም፣ ሲመጣ ድንገት ነው የሚመጣው፣ እድልም አይሰጥም። እንዴት አይነት ዝንጋቴ ውስጥ ቢሆኑ ነው ግን..?!