የለሊት ሶላት እና የአሰጋገድ ሁኔታው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍ሶላት በእስልምና ዋነኛው አሏህ በባሮቹ ላይ የደነገገው ተግባር ነው።
||
የሌሊት ሶላት አንዱ የተረጋገጠ ሱና እና ትልቅ ፋይዳ ያለውና ከምርጥ ኢባዳዎች አንዱ ነው ከሌሊቱ መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ሱብሒ ሶላት ድረስ ከመስገድ በፊት በመጨረሻው አንድ ሶስተኛው ላይ ቢገኝ ይመረጣል።
*
የለሊት ሶላት እና አሰጋገዱ:
✔️ በየሁለት ረከዓው እያሰላመቱ የቻሉትን የፈለጉትን ያክል ይሰግዱና መጨረሻ ላይ አንድ ረከዓ ብቻ በመጨመር በዊትር ያጠናቅቃሉ።
*
የ"ለይል" (ለሊት) ሶላት ተብሎ በውስጥ "ተነይቶ" (ታስቦ) ፋቲሓ ይቀራል።
ከፋቲሓ በኋላ የቻሉትን ሱራ ይቀራል። "ሓፊዝ የሆነ ስው በሒፍዙ አርዝሞ ይቀራል፤ "ሓፊዝ ያልሆነ ስው የሚችለውን ይደጋግማል ካልሆነ ደግሞ ቁርኣን ይዞ መቅራት ይችላል።
በዚህ መልኩ ሁለት ረከዓ ከሰገዱ በኋላ - እንደ "ቀብልያ"፣ "ባዕዲያ" ሱንና ሶላቶች ማለት ነው - አተሕያቱ ቀርተው ማሰላመት ነው።
°
✅ ከዛም በኋላ በዚሁ መስረት የቻሉትን ያክል ሁለት ሁለት ረከዓ እየሰገዱ አስርም ይሁን፣ አስራ ሁለትም፣ አስራ አራትም፣ አስራ ስድስትም፣ ሃያ እና ሃያ ሁለትም ሰግደው መጨረሻ ላይ አንድ ነጠላ ቁጥር በመስገድ ዊትር አድርገው ማጠናቀቅ።
ዊትር ማለት ደግሞ ኢ—ተጋማሽ ቁጥሮች ማለት ነው (1፣3፣5፣7...) ማለትም 1 ረካዓ ሰግደው ተሽሁድን በመቅራት ሶላቱን ዊተር አድርገው ማጠናቀቅ ይችላሉ።
:
እንደው ጠቅለል ሲደረግ ሶላተል-ለይል ማለት ከኢሻ በኃላ እስከ ፈጅር ድረስ ባለው ወቅት ውስጥ የሚሰገድ፣ ቁርአን በዛ ተደርጎ የሚቀራበት ትርፍ የሆነ የሌሊት ሶላት ሲሆን ይህ ሶላት ተራዊህ ወይም ተሀጁድ ተብሎ ሊጠራ ይችላል።
:
ለዛም ነው የሌሊቱ መጀመሪያም ይሁን መካከል ይሁን መጨረሻ ላይ መስገድ ቢቻልም በላጩ ግን የሌሊቱ የመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ላይ መስገድ በላጭ ነው።
*
ምክንያቱም በዚህ ወቅት በሀዲስ እንደተገለፀው አላህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የሚወርድበትና "ማን ነው የሚለምነኝ የምቀበለው⁉️ ማን ነው የሚጠይቀኝ የምሰጠው⁉️ ማን ነው ማሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው⁉️" የሚልበት ሰአት በመሆኑና በርካታ ኡለሞች ዘንድ ከተኙ ቡኃላ ተነስቶ መስገድ በላጭ ስለሆነ ይህን ሱና ለማግኘት ሲባል ነው።
ﻳَﻨْﺰِﻝُ ﺭَﺑُّﻨﺎ ﺗَﺒﺎﺭَﻙَ ﻭﺗَﻌﺎﻟَﻰ ﻛُﻞَّ ﻟَﻴْﻠﺔٍ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺴَّﻤﺎﺀِ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴﺎ ﺣِﻴﻦَ ﻳَﺒْﻘَﻰ ﺛُﻠُﺚُ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﺍﻵﺧِﺮُ، ﻳﻘﻮﻝُ : ﻣَﻦ ﻳَﺪْﻋُﻮﻧِﻲ، ﻓﺄﺳْﺘَﺠِﻴﺐَ ﻟﻪ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴْﺄَﻟُﻨِﻲ ﻓﺄُﻋْﻄِﻴَﻪُ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴﺘَﻐْﻔِﺮُﻧﻲ ﻓﺄﻏْﻔِﺮَ ﻟﻪ؟
ﺍﻟﺮﺍﻭﻱ : ﺃﺑﻮ ﻫﺮﻳﺮﺓ - ﺍﻟﻤﺤﺪﺙ :
ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺻﺤﻴﺢ
📒ﻣﺴﻠم (758)
በተጨማሪም ይህ የቁርአን አንቀፅ የሚያመለክተው ሁሉንም የሌሊት ሶላቶች ነው።
”وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا“
"ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በርሱ (በቁርአን) ስገድ፣ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል።"
📒ሱረቱል ኢስራእ [79]
*
በመጨረሻም እስከ ሌሊቱ አጋማሽ በሗላ (ማለትም ከ 7 ሰዐት በሗላ) እንቅልፍ በተለያዩ ስራዎችና ምክንያቶች ሳትተኙ ከቀራችሁ ሁለት ረካዓና አንድ ውትር ወትራችሁ ሀጃም ያላችሁ ዱዓችሁን አድርጋችሁ ብትተኙ ለስኬታችሁ ቁልፍ፣ ለኢማናችሁ ትርፍ፣ ወንጀልን ለማርገፍ፣ ለጭንቃችሁ መውጫ እና ከአላህ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማጠናከር የተመረጠ ግዜ ነውና ተጠቀሙበት።
||
ይህንን ያነበባችሁ ወንድምና እህቶች በሙሉ:-
ሌሎች አንብበው ከሰገዱ የአጅሩ ተካፋይ ናችሁና፤ መልክቱን ለሌሎችም እንዲደርስ ሁላችሁም
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.