Translation is not possible.

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

«ዘመዴ የሆነችን ሴት ማግባት በሸሪዓው እንዴት ይታያል?።» ብሎ ለጠየቀ ሰው የተሰጠ ምላሽ።

በአንዳንድ ብሔረ-ሰቦች ዘንድ በራሳቸው ልምድና ባህል መነሻነት፣ሸሪዓ የፈቀደውንና በቁርዓን ከተከለከሉት ዝርዝር ውስጥ የማይካተተውን የዘመዳሞችን መጋባት ከመቃወም አልፎ፣ጭራሽ የተጋቡትን እስከማፋታት ድረስ የሚደርስ እጅግ አደገኛና አላህ ሀላል ያደረገውን እነርሱ ሀራም ለማድረግ የሚዳዳቸው፣አዋቂ ነኝ የሚሉ ግን ያለማወቅን ኩታ ያጣፉ የጎሳ መሪዎች በብዛት ይስተዋላሉ።በመሰረቱ ኒካህን የደነገገልን አላህ፣ሸሪዓውን ያብራሩልን ነብይም፣አንድ ሰው ሊያገባቸው እርም የሚሆኑበትን ሴቶች ዝርዝር ነግረውናል።ከተዘረዘሩት ውጭ የተቀረው ሁሉ መስፈርቱ ተጠብቆ፣ሸሪዓው እስከፈቀደልህ ቁጥር ድረስ ለማግባት ሀላል ነው።ነገር ግን እኛ እንደ ማ/ሰብ ጭራሽ በአያት ኣሊያም በቅድመ-አያት የሚገናኙትን ብቻ ሳይሆን፣በሰባተኛ አያትም ከተገናኙ መጋባታቸውን ይቃወማሉ።ነገር ግን በሸሪዓችን የአጎትን ልጅ ወይም የአክስትን ልጅ ማግባት እንደሚቻል በቁርዓንም ሆነ በሐዲስ ተነግሮ እናገኛለን፣ተተግብሯልም።ነቢዩ ለአሊይ ልጃቸውን ፋጢማን ድረውታል።በሌላ በኩል የአጎታቸው የአባስ ልጅ መሆኑን አትርሱ።ለራሳቸው ዘይነብ ቢንት ጀሕሽን አግብተዋል።በአባት የአክስታቸው የኡመይማ ቢንት አብዲልሙጠሊብ ልጅ ናት።ቁርዓንም በግልፅ ለነቢዪ የሚከተለውን ብሏቸዋል፦ «አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፣ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች፣ እነዚያንም ከአንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹማህንም(በእናትህ በኩል አጎትህ)ሴቶች ልጆች፣ የየሹሜዎችህንም(በእናትህ በኩል አክስትህ) ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ ፈቅደንልሃል፡፡» አል-አሕዛብ : 50።እኛ ግን ብዙም ስላልተለመደ፣አንድ ሰው የአጎቱን ልጅ ቢያገባ ዝምድና ቆረጠ ብለን መደንፋት ነው ስራችን።ለመሆኑ ይሄንን አንቀፅ አስተውለነው እናውቅ ይሆን?፦

«ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ በደለኞችም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አልላቸው፡፡» አሽ-ሹራ : 21።

እንግዲህ የፈቀድኩትን አይፈቀድም የሚሉ ወየውላቸው እያለን ነው አላህ። ያረብ ከቁጣህ በአንተ እንጠበቃለን።

ኢንሻአላህ በቀጣይ ፖስት ሙሉ በሙሉ ሀራም የሆኑ፣ነገር ግን እንደ ሀላል የሚታዩና የተለመዱ የጋብቻ አይነቶችን በወፍ-በረር እናያለን።

አቡ አብዲላህ አልወራቢይ፣

አልመዲነቱል-ሙነወረህ፣

ጁማደልዑላ 7/1445 ዓ.ሂ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group