Тарҷума мумкин нест.

Follow Share → Umma ሚዲያ

↓↓↓↓↓

Umma ሚዲያ

#ሐብታም ብትሆን፣ የምትጠራው ሐብታም #ሰው ተብለህ ነው።

#የተማርክም ከሆንክ፣ የምትጠራው የተማረ #ሰው ተብለህ ነው።

#ቀይም ብትሆን፣ ቀዩ #ሰው ነው ምትባለው።

#ቆንጆም ብትሆን፣ ቀንጆ #ሰው ነው ተብለህ ምትጠራው። ከነዚህ አይነት ሰዎች አንዱም ብትሆን በየትኛውም መልኩ ከሰውነት አትወጣም።

#ልብ በል! እነዚህ ከላይ #ሰው ከሚለው ቃል በፊት የተቀመጡት ስሞች ሰው ከሆንክ በሗላ የተቸሩህ እንጅ ሰው ከመሆንህ በፊት የተሰጡህ ፀጋዎች አይደሉም።

ከጊዜ በኃላ የተሰጡህን ነገሮች ደግሞ በጊዜ ምክንያት ልታጣቸው ትችል ይሆናል። በየትኛውም መልኩ ግን ሰውነትህን ሊነጥቅህ የሚችል ማንም የለም።

#ሁሉም ሰው ሲማር ሙሁር ሳይማር ሲቀር መሃይም ነው።

#ሁሉም ሰው ከሰራ ሐብታም ካልሰራ ደሃ ነው።

#ሁሉም ሰው ሲደላው ያምርበታል ሲቸግረው ያስጠላበታል።

#ሁሉም ሰው ፀሐይ ሲበዛበት ይጦቅራል። አየሩ ሲመቸው ይቀላል። ስለሆነም፥

#ሁሉም ሰው ከአደም ነው።

#ሁሉም ሰው እኩል እናቱ መሃፀን ውስጥ ለዘጠኝ ወር ነው የተረገዘው።

#ሁሉም ሰው ከአንድ ፈጣሪ ነው።

#ሁሉም ሰው የሚበላው ምግብ፣ የሚጠጣው መጠጥ የሚያስፈልገው ከመሆኑ ጋ የበላውንና የጠጣውንም ነገር የማስወገድ ግዴታ አለበት።

#ሁሉም ሰው ታማሚም ሟችም ነው። ወዘተ...

#ሰው ምንም ወደላይ ቢንጠራራ ከሰውነት ተራ ወጥቶ መላዕክ ሊሆን አይችልም።

#ምንም ቢቸገርና ቢጎሳቆል ወደ እንሰሳነት ሊወርድ አይችልም።

#ሰው በየትኛውም መልኩ ሰው ነው!

አላህ የሰውን ልጅ ከሁሉ አልቆታልና፤ ሰውም ሰውን እኩል ሊያይና ሊያከብር ግድ ይለዋል! በመጨረሻም ይህችን ግጥም ተጋበዙልኝ!

👇

#የሰው_ዛፍ

ምነው የሰው ልጆች፣ ልዩነት መረጡ፣

ከአንድ ዛፍ በቅለው፣ መበላለጥ ሻቱ፣

ያ'ንድ ዛፍ ቅርንጫፍ፣ ስሩ አንድ መሆኑን፣

ማየት ተስኗቸው፣ ዘንግተውት ይሆን?

ያ'ንድ ዛፍ ፍሬዎች፣ ሁሉም አንድ አይነት ነው።

ማንጎ ሎሚን ማፍራት፣ የማይታሰብ ነው።

ዛፉ ማንጎ ከሆን፣ ፍሬውም ማንጎ ነው፣

ዛፉ ሰው ከሆነም፣ ፍሬውም ያው ሰው ነው።

ምናልባት አንዱ ሰው፣ ካ'ንዱ የሚበልጠው፣

አላህን በመፍራት፣ ብቻና ብቻ ነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group