Translation is not possible.
ዚክር → አላህን ማውሳት‼
===================
✍ ጊዜ ከማይገድባቸው ዒባዳዎች መካከል አንዱ ዚክር ነው።
የታክሲ ሰልፍ ላይ የምናሳልፈውን ጊዜ፣ የሆነ ጉዳይ ለማስፈጸም በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም ሌላ ተቋም ወረፋ ስንጠብቅ የምናሳልፈውን ጊዜ፣ ወደ ሥራ ቦታ ስንሄድም ሆነ ስንመለስ መንገድ ሲዘጋጋ መንገድ ላይ የሚያልፈውን ጊዜ፣ ተማሪ ከሆንን የረፍት ሰዓትና መምህር እስኪገባ ድረስ የምናሳልፈውን ጊዜ፣ ነጋዴና ሠራተኛ ከሆንን ደንበኛ እስኪመጣ ድረስ የሚያልፈውን ጊዜ፣ የቤት ሠራተኛ የሆነ ሥራውን በአካሉ እየሠራ በምላሱ… ዚክር በማድረግ ብናሳልፈው እጅግ በጣም አትራፊዎች ነን።
 
ከተለያዩ ወቅቶችና ሁኔታዎች ከተያያዙት ዚክሮች ባሻገር በየትኛውም ወቅት ዚክር ማድረግ እንችላለን። አላህን በማስታወስ ልቦች ይረጋሉ።
 
አላህ እንዲህ ይለናል፦
 
 
(الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ)
 
«(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡»
[አ-ር'ረዕድ: 28]
 
*
 
 
(… وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا)
 
«… አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡»
[አል-አሕዛብ: 35]
*
 
 
(الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ)
 
«(እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡»
[ኣሊ ዒምራን: 191]
*
 
ውዱ ነቢያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
(مَثَلُ الذي يَذْكُرُ رَبَّهُ والذي لا يَذْكُرُ رَبَّهُ، مَثَلُ الحَيِّ والمَيِّتِ.)
«ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ አምሳያው፤ ልክ እንደ ሕያውና ሙት ነው።»
[አል-ቡኻሪይ: 6407፣ ሙስሊም: 779]
*
ስለዚህ አላህን የምናወሳ ሕያው እንሁን።
አላህ ያግራልን‼
||
t.me/MuradTadesse
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group