Terjemahan tidak mungkin.

☞የባለቤትሽን ቤተሰቦች ትወጃለሽ?? እህቴ

☞ሙእሚን ሴት፤ የባሏን ቤተሰቦች በተለይም እናቱን ታከብራለች። መልካም ግንኙነትንም ታበለፅጋለች። የባልን እናት እንደጠላት የሚስለውን ያረጀ ግንዛቤ ወደጎን በመተው አላህን ታስደስታለች። ችግር ቢገጥማት እንኳ ሰብር በማድረግ የባለቤቷን ሀቅ ትሞላለች።

✅መልካም ሚስት ባሏ ለእናቱ መልካም እንዲሰራ ትረዳዋለች፤ እናቱን በመንከባከብና ሀቋን በመሙላት ረገድ ድክመት ካየችበትም ትመክረዋለች እንጂ ለሸይጣን ረዳት አትሆንም!!

☞ውዷ እህት! በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ለአላህ ብለሽ የባለቤትሽን ቤተሰቦች ጠይቂ። ከዚህ ቀደም የተቀያየምሽውን ሁሉ ይቅር ተባባይ። አላህን እና ባለቤትሽን በማስደሰትሽ የምታገኚው የመንፈስ እርካታ በገንዘብ የማይተመን እንደሆነ ትረጃለሽ።

አላህ ላገቡት ያማረ የፍቅር የደስታ ሂወት ያድርግለችው ላለገቡት ኸይረኛውን ይወፍቃችው

‼️ዱንያ አጭር ህይወት ናትና በፅድቅ እናሳልፋት✅

✅ቴሌግራማችን

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam

╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam

Hantar sebagai mesej
Kongsi di halaman saya
Kongsi dalam kumpulan