Наган дахаан йохтахам.

እዚህ ምድር ባሉ ነገሮች ላይ ጥገኛ ሁነን የሆነ ሰዐት ካልተሳካልን ልክ ጠረጴዛችን ጠርዝ ላይ የነበረ የአበባ ማስቀመጫ ወድቆ ከተሰባበረ ዳግመኛ ሊጠገን እንደማይችለው የኛም ነገር እንደዛው ይሆናል ።ይሁን እንጂ የመሬት ስበት ለአበባ ማስቀመጫው መሰበር እንደሌለበት ሁሉ ለኛም መሰበር ጥገኛ የሆንባቸው ነገራት መወቀስ የለባቸውም ። እኛ ልንደገፍ እና ሙሉ ክብደታችንን ልናሳርፍ የሚገባው በአሏህ ብቻ ነው ።

{فَمَن يَكۡفُرۡ بِٱلطَّٰغُوتِ وَيُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ فَقَدِ ٱسۡتَمۡسَكَ بِٱلۡعُرۡوَةِ ٱلۡوُثۡقَىٰ لَا ٱنفِصَامَ لَهَاۗ }

[በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በርግጥ ጨበጠ]....(አልበቀራ ፡ 256)

Send as a message
Share on my page
Share in the group