Translation is not possible.

🍂የ100 ወይስ የ10 ብር ትርፍ?

<<ብቻህን ብትሆም በሃቅ ላይ እስከሆንክ አትጨነቅ።>>

ይህ ሀሳብ ገዢ ነው። ነገር ግን ሁሌም ብቻህን ከሆንክ እና አንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች ቁጥር ሁሌም እየተመናመነ ከሆነ ዙሪያህን ተመልከት፣ አካሄድህን አጢን። የጎደለኝ ነገር ይኖር ይሆን?  ብልህ እራስህን ተመልከት። አካሄድህ ሃቅ ቢሆንም እንኳን ለኡማው የምታደርስበት መንገድ ምን እንደሚመስል አስተውል። ከሰለፎች አንፃር የዳዕዋ አጀማመርህ እና አካሄድህ ምን አይነት ሚዛን ላይ እንደሆነ ተመልከት። ፈረስ ለመጋለብ ካሰብክ የኮርቻውን መፈናጠጫ መርገጥህን ማረጋገጥ ግድ ይላል። ዳዕዋ የምታደርግላቸውን ሰዎች ሁኔታም ማጤን እንደዚሁ ነው። በሃላል መንገድ የ100 ብር ትርፍ ያለበት ገበያ ትተህ የ10 ብር ትርፍ ለማትረፍ የምትኳትን ከሆነ ሞኝ ወይም እብድ ከመሆን አታልፍም። በአጭሩ ዙሪያህን ሳታጤን፣ ማድረስ ያለብህን ሰበቦች ሳታደርስ ብቻዬንም ብሆን ሃቅ ላይ እፀናለሁ! ማለት ትክክል አይሆንም። ለዚህም ነው አምላካችን አላህ በሱራ አል–ዒምራን፣ ቁጥር 104 እና 105 ላይ: <<ከእናንተ ወደ በጎ ነገር የሚጣሩ፣ በመልካም ስራ የሚያዙ፤ ከመጥፎም ተግባር የሚከለክሉ ህዝቦች ይኑሩ። እነዚህ ፈላህ የሚወጡ ናቸው። እንደነዚያም ግልፅ ማስረጃ ከመጣላቸው በኋላ የተለያዩና የተጨቃጨቁ እንደሆኑት አትሁኑ። ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለላቸው።>> ያለው

<<اللبيب تكفيه الإشارة>>

"ብልህ የሆነ ሰው ጥቆማ ትበቃዋለች"

✍ አቡ ሁዘይፋህ’

https://t.me/nurmesjed

Telegram: Contact @nurmesjed

Telegram: Contact @nurmesjed

You can view and join @nurmesjed right away.
Send as a message
Share on my page
Share in the group