ደስተኛ ነህ❓ ደስተኛ ነሽ❓
ደስታስ ምን እንደሆነ እናውቀዋለን?
ደስታ ሁሉም የየራሱ ፍቺ የሚሰጠው ቢሆንም ጠቅለል ስናደርገው ግን: ደስታ ማለት:— "ተከታታይና የማይቋረጥ የሆነ ውስጣዊ መዝናናት፣የተረጋጋ የውስጥ ስሜት፣ሐሴት ማድረግ ሲሆን፥ይኸውም የሚገኘው በሀያሉ ፈጣሪ አላህ እና ከሞት በኋላ ባሉ ፀጋዎች በማመን፣ከመልካም ስብዕና፣መልካም ነገሮችን አዘውትሮ ከማድረግ፣ለስኬት ከበቃች ሕይወት፣ እንዲሁም የመጨረሻ ሕይወት እጣ ፈንታ ማማር የሚገኝ የእርካታ ጫፍ ነው"።
ታድያ ይህንን ደስታ ለማግኘት ሰዎች ብዙ ውጣ ውረዶችን ያልፋሉ፣ብዙ መሰናክሎችን ይጋፈጣሉ፣ አያሌ ዘዴዎችን ይዘይዳሉ፣የምክር አግልግሎቶችን ይታደማሉ። ደስታም በሃብት፣ በስልጣን፣በፖለቲካ፥በእስፖርት፥በሳይንስ፣ዝነኛ በመሆን፣በትምህርት ጥሩ ውጤትን በማስመዝገብ ይፈልጉታሉ። አንዳንዶች ደግሞ ደስታ ዱርዬ መስሏቸው በየመጠጥ ቤቱ፣ በየጭፈራ ቤቱ፣በየዝሙት ቤቱ ይፈልጉታል ግን ደስታ ዱርዬ አይደለም። ይህ ሁሉ ልፋታቸው ግን ደስተኛ ሊያደርጋቸው አይችልም። ምክንያቱም የጎደላቸው አንድ መስፈርት አለና። እርሱ በሃያሉ አምላክ አላህ ማመን እና ለእርሱም ትእዛዛት ማደር ነው።
አላህም እንዲህ ይላል:
﴿مَن عَمِلَ صالِحًا مِن ذَكَر أَو أُنثى وَهُو مُؤمِن فَلَنُحيِيَنَّه حَياة طَيِّبَة وَلَنَجزِيَنَّهُم أَجرَهُم بِأَحسَن ما كانوا يَعمَلون﴾ (النحل٩٧)
ትርጉም: ከወንድም ከሴትም አምኖ ከዛም መልካምን የሰራ ያማረችን ህይወት እናኖረዋለን፣ይሰሩትም ከነበረው በተሻለ አንመነዳቸዋለን። [አል ነህል 97]