Translation is not possible.

"አቤት ማማራቸው"

እንደው ጉድ ያሰኘው ይኸው ውበታቸው፤

እነሱን ለማየት ሰዎች ጉጉታቸው፤

'አቤት ብዛታቸው ጥቁር ነው ልብሳቸው፤

ጥግ ጥጉን ይዘው ሲሄዱ ላያቸው፤

እነዚህ እንስቶች አቤት ማማራቸው፤

ማለቱ ስሰማ እኔም ወደድኳቸው፤

ከላይም እስከታች አሸፋፈናቸው፤

ሲሄዱ በመንገድ አረማመዳቸው፤

ድምፅም አይሰማ ላነጋገራቸው፤

የሰለፍይ ሴቶች አቤት ማማራቸው፤

ምን ይሆን ሚስጥሩ የመሸፈናቸው፤

በሀያእ በአዳብ የመራመዳቸው፤

ሲያወሩ ድምፅን ዝቅ ማድረጋቸው፤

ብለው ተገረሙ ሰዋች ሲያዩዋቸው፤

ሚስጥሩ ወዲህ ነው እኔ ልንገራችሁ፤

በነዚህ እንስቶች ለተገረማችሁ፤

የአላህን ትዛዝ የነብዩን ሱና፤

በነዚያ ቀደምቶች በሰለፎች ፋና፤

ሆኖ ነው ኑሮቸው እንዲህ የተቃና፤

በልባቸው ሰርፆ የአላህ ፍራቻ፤

የነብዩን ሱና ይዘው በክራንቻ፤

ግባቸው ሆኖ ነው ሁሌም ጀነት ብቻ፤

ለዚህ ነው ያማሩት የሌላቸው አቻ፤

እህቴ ካማረሽ ክብርት መሆንን፤

ወንድሜም ከፈለክ ንግስት ማግባትን፤

በሀያእ ተክነሽ ልበሽው ሒጃቡን፤

አንተም አስለብሳት ለውዷ እህትህ፤

ስታገባም ምረጥ ባለ ዲንዋን ብለህ፤

አባዬም አስለብስ ያንተው ውድ ልጅህ፤

ጥብቅም እንድትሆን ስምህ ልታስጠራህ፤

እንልበስ ባንድነት ሒጃቡን በጋራ፤

በሱሪ በሚን እንዳንሆን ፋራ፤

በኒቃብ በጅልባብ ይሁን ጉዞኣችን፤

ለዱንያም ሰላም ላኸራም ቤታችን!!!

منقول

https://ummalife.com/umma1698228713

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group