አደራህን
ለበሽተኛ ተስፋ ሰጪ እንጂ ተስፋ አስቆራጭ አትሁን!
አንድ ሰው የሆነ የታመመን ሰው ለመጠየቅ ይሄዳል።ጥቂት ከተቀመጠም በኋላ ታማሚውን በሽታው ምን እንደሆነ ይጠይቀውና የታመመበትን በሽታ ይነግረዋል። በእርግጥ በሽታው ትንሽ ከበድ ያለ ነበር። የበሽታውን አይነት የሰማው ጠያቂም ጩኸት ጀመረ ኡኡኡ.........ውይ ውይ ውይ.....እንዴ...እንዴ....እንዴ.... ይህ በሽታ እኮ ጔደኛዬ ተንገላቶ የሞተበት በሽታ ነው! ኸረ ምን ጔደኛዬ ብቻ የወንድሜስ ጔደኛ....አከሌንም......አከሌንም..... ያረገፈ በሽታ ነው እኮ ወይ ወንድሜን! እያለ ያቀልጠው ቀጠል በሸተኛው በጭንቀት ጭንቅላቱ ሊፈነዳ ቀረበ.........ሱብሀነሏህ! ምነው አፉን በያዘ!?
ታዲያ አያልቅ የለምና ወሬውንም ጥየቃውንም ይጨርሳል። ከቤቱ ሊወጣ ሲል ወደ በሽተኛው ዞር ይልና፦
የምትነግረኝ ኑዛዜ ይኖርሀልን? ሲል ይጠይቀዋል።(መሞቱ እንደማይቀር ማርዳቱ ነበር)
ህመምተኛውም አዎን ኑዛዜ አለኝ እሱም፦(አሁን ከዚህ ከወጣህ በኋላ ሁለተኛ ወደዚህ እንዳትመለስ ነው)ይለዋል።
እባክዎን በሽተኛን ሲጠይቁ ስለ ሞት አያንሱ!
አደራዎን ተስፋ ሰጪ እንጂ ተስፋ አስቆራጭ አይሁኑ!