Translation is not possible.

#አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረ.ዐ) እንደነገረን #ረሱል እንዲህ አሉ፡-#አላህ የጀነት ነዋሪዎችን እንዲህ ይላቸዋል፡- የጀነት ነዋሪዎች ሆይ! እነሱም፡- አቤት ጌታችን ሆይ! ሁሌም ለጥሪህ ታዛዦች ነን፡ ረዳታችንም አንተው ነህ ይላሉ፡፡ እሱም፡- በሰጠኋችሁ ጸጋ ተደሰታችሁን? ሲላቸው፡ እነሱም፡- ከዓለማት ለማንም ያልሰጠኸውን ጸጋ ሰጥተኸን እንዴት አንደሰትም! በማለት ይመልሳሉ፡፡ አላህም፡- ከዛ የበለጠ ነገር ልሰጣችሁ ነኝ! ሲላቸው፡ እነሱም፡- ጌታችን ሆይ! ከዚህ የበለጠ ምን ጸጋ ኖሮ ነው? በማለት ይጠይቃሉ፡፡ እሱም፡- ውዴታዬን በናንተ ላይ አሰፍረዋለሁ፡ ከዚህ በኋላ ለዘልዓለም አልቆጣባችሁም ይላቸዋል" (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት)፡፡

ዐብዱላህ ኢብኒ መስዑድ (ረ,ዐ) እንዲህ ይላል፡-#ረሱል (ﷺ) ጋር (በሚና) ድንኳን ስር እያለን እንዲህ አሉን፡-#የጀነት ሰዎች ሩብ እናንተ ብትሆኑ #ትወዳላችሁን?›› አዎን! አልናቸው፡፡ በድጋሚ ‹‹የጀነት ሰዎች 1/3 እናንተ ብትኾኑ ትወዳላችሁን?›› ሲሉን፡ አዎን! አልናቸው፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ ‹‹የጀነት ሰዎች ግማሹ እናንተ ብትኾኑ ትወዳላችሁን?›› ሲሉን አዎን! አልናቸው፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹የኔ ነፍስ በእጁ በሆነችው በአላህ እምላለሁ፡፡ እናንተ የጀነት ሰዎች ግማሹ እንደምትሆኑ ባለ ሙሉ ተሰፋ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ጀነትን ሙስሊም የሆነ ነፍስ እንጂ ሌላው አይገባትምና›› አሉ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

🌺 @suhabaa 🌺

━━━━━🍃🌸🍃━━━━━

┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄

✍ሙሀመድ

Send as a message
Share on my page
Share in the group