Translation is not possible.

አሳፋሪ ነው‼

==========

(የእሸቱ መለሰ አሳፋሪ ንግግርና የሙስሊሞችን እምነት የማስቀየር የረጅም ጊዜ እቅድ!)

||

✍ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ በመባል የሚታወቀው ግለሰብና ዶንኪ ቲዩብ የሚባል ቻነል ያለው ግለሰብ በብዙዎች ዘንድ መልካም ሰው ነው ተብሎ የሚታሰብ ሰው ነበር። ግን የእንዲህ አይነት ግለሰቦች መልካምነት ጭምብላቸው እስኪገለጥ ድረስ ብቻ ነው።

ተከታይና ዝና እስኪያተርፉ ድረስ ከዚያም ከዚህም አለን እያሉ ካካበቱ በኋላ፤ መጨረሻ ላይ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ጭምብላቸው ይገለጣል።

ሰሞኑን ወደ ሃገረ ኳታር ዶሓ ከተማ አቅንቶ በቀጥታ ስርጭት ለቤተ ክርስቲያን መገንቢያ እያሰባሰበ ነበር። (እንደ ዐረብ ኢሚሬትና ኳታር ያሉ የዐረብ ሃገራት በብዝሃነትና አካታችነት ሽፋን ተበክለዋል።) 

በዚህ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሙ ላይ ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ ሲያነሳሳ፤ «ያው እንደምታውቁት የዚህ ሃገር ዜጎች እምነት ይታወቃል። (ሙስሊም ናቸው ማለቱ ነው።) ቤተ ክርስቲያኑን የመገንባት አላማችን ለኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ነገ ጧት ለዓለምና (ሙስሊሞቹም) ክርስትና የሚነሱበት፣ የሚጠመቁበት፣ ንስሐ የሚገቡበት፣ ስጋ ወደሙ የሚቀበሉበት ነው።» የሚል ይዘት ያለው ንግግር በይፋ ተናግሯል።

(ንግግሩን ቃል በቃል ከራሱ አንደበት በቪድዮ በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ።

https://t.me/MuradTadesse/32772)

ይህ የኩፍር ጥሪ ነውር ነው። ቢሳካለት ኖሮ ሙስሊሞችን እምነታቸውን ለማስለቀቅና ወደርሱ እምነት መቀላቀል ዋና አላማው እንደሆነ ንግግሩ ይመሰክራል። እንዲህ አይነቱ ግለሰብ የሙስሊም በሚባል ሃገር ሂዶ እንዲህ አይነቱን ድፍረት የተሞላበት ንግግር ከተናገረ፤ እዚህ ሃገራችን ውስጥ በስውር ሙስሊሙን እምነቱን ለማስለቀቅ የማይሠራ ሰው ስላለመሆኑ ማረጋገጫ የለም።

ከላይ ሲታዩ ሁሉንም አቃፊ ይመስላሉ። ውስጣቸው ግን ጋሬጣ ነው። በርግጥ ውስጠ አዋቂው አላህ ስለማንነታቸው በቅዱስ ቃሉ በቁርኣን ላይ በግልፅ እንዲህ ሲል ነግሮናል፦

(وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ)

«አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ኃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡»

[አል-በቀራህ: 120]

*

ለማንኛውም አቅሙ ያላችሁ ኳታር የምትገኙ ወንድምና እህቶች ይህን የግለሰቡን ንግግር በዐረብኛ የግርጌ ትርጉም አያይዛችሁ ለሚመለከታቸው አካላት ብታቀርቡትና ምናልባት የሚገባቸው ከሆነ እነዚህ ግለሰቦች ያላቸውን የሃገሪቱን ዜጎች እምነት የማስቀየር የረጅም ጊዜ እቅድ እንዳላቸው ጠቁማችሁ ከወዲሁ መቅጨት ቢቻል የተሻለ ነው።

አሊያ እግር ከዘረጉ እዛም ሂደው በለመደው አፋቸው «ኳታር የክርስቲያን ደሴት ናት!» ሊሉ ይችላሉ። የእስራኤል አይሁዳዊያን መላው ዓለም ተጠይፏቸው መግቢያ መውጪያ ሲያጡ ወደ ፈለስጢን ምድር ሂደው በጥገኝነት ተጠልለው ሳሉ፤ ቀስ በቀስ ባላባቱን ፈለስጢናዊ ጭሰኛ አድርገው ይሄው ስቃያቸውን እያሳዯቸው ነው።

በተረፈ ግን በእኛው በሙስሊሙ ታዳሚና ተሳታፊ ጭምር በዩ ቲዩብ ዶላር እየሸቀሉ እምነታችንን እስከማስቀየር ድረስ ከሚያሴሩልን ግለሰቦች የዩ ቲዩብ ቻነል ለቅቃችሁ ብትወጡ የተሻለ ነው። ጠላቶቻችንን መጥቀም የለብንም። ለነርሱ ሴራ ማበረታቻ መሆን የለብንም። Unsubscribe, Unfollow, Unlike, block በማድረግ ከገፃቸው እንውጣ። በምትኩ የንጹሕ ሰዎችንና ዲናችንን የሚያስተምሩ ጠቃሚ ገፆችንና ሚዲያዎችን እንከታተል።

ለ1 መስጂድ ሚናራ ገቢ አሰባሰብኩ ይባልና ለ100 ቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንድትሳተፍ የሚያመቻች ብልጥ።መሳይ ያልተነቃበትና ሚዛናዊ መሳይና አስመሳይ ሰው ነው የሚመስለኝ። በጊዜ ቢነቃበት ጥሩ ነው። ዝም ብላችሁ በጭፍን አትደግፉ። እርግጥ ነው ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ እያሰባሰብ ስለ ሙስሊም መልካምነት እንዲያወራ ባይጠበቅም፤ ግን የዚህ ንግግሩ አውድና ይዘት ከጀርባ ያለውን እኩይ አላማና ውስጣዊ እሳቤ ምን እንደሆነ ይጠቁማል።

3 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group