1 year Translate
Translation is not possible.

እስራኤል በጦር ወንጀል እንድትከሰስ ክስ ቀረበባት

November 18, 2023

የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት በፕሪቶሪያ ያለው የእስራኤል ኢምባሲ እንዲዘጋ ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጿል

እስራኤል በጋዛ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በጦር ወንጀል እንድትከሰስ ክስ ቀረበባት።

ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከተጀመረ 43ኛ ቀኑን ይዟል።

እስራኤልም ራሴን ለመከላከል በሚል የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ ጋዛ ላይ ድብደባ ከጀመረች 43 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፤ በእስራኤል ጦርና በሃማስ ታጣቂዎች መካከል የተቀከቀሰው ጦርነትን እንደቀጠለ ይገኛል።

በርካታ ሀገራት እስራኤል የጀመረችውን ጥቃት እንድታቆም ግፊት በማድረግ ላይ ቢሆኑም በጋዛ ላይ እየደረሰንያለው ጥቃት ግን እንደቀጠለ ነው።

እስራኤል ጥቃቷን አለማቆሟን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ ጉዳዩን ወደ ጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መውሰዷን አስታውቃለች።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ እንዳሉት "እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ እያደረሰች ላለው ጥቃት ልትጠየቅ ይገባል" ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት ጉዳዮን እንደሚመረምር እና የእስር ማዘዣ እንደሚያወጣ እናምናለንም ሲሉ ፕሬዝዳንት ራማፎዛ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የደቡብ አፍሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት በፕሪቶሪያ ያለው የእስራኤል ኢምባሲ ይዘጋ በሚለው ጉዳይ ዙሪይ ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ከኢምባሲው በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ከእስራኤል ጋር ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥም ይወያያል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ምክንያት ከ11 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ሲገደሉ ሁለት ሺህ ገደማ እስራኤላዊያንም መገደላቸው ተገልጿል።

አሜሪካ ለእስራኤል በቀጥታ የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን ኢራን፣ ቱርክ፣ ኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ደግሞ ሀማስን በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ይደግፋሉ ተብሏል።

አረብ ኢሚሬትስ በጋዛ የቆሰሉ ህጻትንና ቤተሰቦቻው ተቀብላ ወደ ሀገሯ ማስገባት ጀመረች

በጋዛ የቆሰሉ 15 ህጻትንና ቤተሰቦቻውን የያዘ የመጀመሪያው አውሮፕላን አረብ ኢሚሬትስ አዱ ዳቢ ገብቷል።

ተጎጂዎችን ይዞ ከግብጽ አል አሪሽ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው አውሮፕላን አዱድሃቢ መድረሱንም የአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ተጎጂዎቹ ወደ አረብ ኢምሬትስ የተጓዙት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን እንዲስተናገዱባቸው ባሳለፉት ውሳኔ መስረት ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group