Translation is not possible.

ደቡብ አፍሪካ ከጋዛ ጥቃት ጋር በተያያዘ እስራኤልን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት መውሰዷ ተገለጸ

****************************

ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ እየወሰደች ባለችው እርምጃ አገሪቱን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) መውሰዷን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አስታወቁ።

የእስራኤል መንግሥት በጋዛ እየፈጸመ ያለው ተግባር በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት መዳኘት እንዳለበት ከበርካታ አገራት ጋር መግባባታቸውን ፕሬዚዳንቱ መግለጻቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

በእስራኤል ጋዛ ጦርነት እስራኤልን አጥብቆ በመተቸት እና ለፍልስጤማውያን ግልጽ ድጋፍ እየሰጡ ካሉ ጥቂት አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ነች።

የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (አይሲሲ) እንደ ጦር ወንጀል እና ዘር ማጥፋት ባሉ ክሶች የተከሰሱ ግለቦችን የሚዳኝ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group