Translation is not possible.

አተህያቱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ነብያችን”ﷺ” በለይለቱል ኢስራ ወል ሚዕራጅ ጉዞዋቸዉ ወቅት አላህ ሲገናኙ እንዲህ ነበር ያሉት’’

አተህያቱ ሊላሂ ወሰለዋቱ ፤ ወጠይባ’’ التَّحِيَّاتُ لِلّٰهِ وَالصَّلَوَاتُ وَالطَّيِّبَاتُ،

ማለትም ’’ክብር ሁሉ ለአላህ ነዉ፤ ሶላቶች እና መልካም ተግባራቶችም ለአላህ ሲባል የሚደረጉ ናቸዉ" አሉ።

አላህም መለሰላቸዉ፦ ’’አሰላሙ አለይከ አዩሃ ነቢዩ ወራህመቱላሂ ወበረካቱ" اَلسَّلَامُ عَلَيْكَ أَيُّهَا النَّبِيُّ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ، ማለትም ’’አንተ ነብይ ሆይ! ሰላም በአንተ ላይ ይዉረድ፡፡ የአላህ እዝነትና ዉዴታም ይስፈንብህ"

ነብያችን”ﷺ” እንዲህ በማለት መለሱ፦ "’አሰላሙ አለይና

ወዐላ ዒባዲላሂ አሷሊሒይን’’´ اَلسَّلَامُ عَلَيْنَا وَ عَلٰى عِبَادِ اللهِ الصَّالِحِيْنَ، ማለትም "በእኛ እና በአላህ ቅን ባሪያዎችም

ላይ ሰላም ይስፈን"

ይህንን የሰላምታ ቃለ-ምልልስ እየሰሙ የነበሩ መላእክቶች እንዲህ አሉ፦

’’አሽሃዱ አን ላ ኢላሃ ኢለላህ ወአሽሃዱ አነ ሙሃመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ’’ أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلٰهَ إِلَّا اللهُ، وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَ رَسُوْلُهُ ማለትም "ከአላህ ዉጪ ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልእክተኛዉ እነደሆነ አመሰክራለሁ"፡፡

እንግዲህ ይህ ነዉ በጌታችንና በነብያችን”ﷺ” መካክል የተደረገዉ የሰላምታ ልዉዉጥ፡፡ጥበብ የተሞላበት የነብያችን”ﷺ” ኡመትን ሁሉ ያካለለ ቅዱስ ንግግር ነዉ፡፡ ልብ ብላችሁ ከሆነ አላህ ’’አንተ ነብይ ሆይ! ሰላም በአንተ ላይ ይዉረድ፡፡ የአላህ እዝነትና ዉዴታም ይስፈንብህ" ሲላቸዉ፤ እርሳቸው "በእኛ እና በአላህ ቅን ባሪያዎችም ላይ ሰላም ይስፈን" ነበር ያሉት፤ ነቢያችን በእኔ ላይ ሰላም ይስፈን አላሉም ይልቁንስ በእኛ የሚለዉን ቃል ነዉ የተጠቀሙት፡፡

ትርጉሙን የማታዉቁ ሰዎች ከአሁን በኃላ ኢንሻላህ እንዲህ አይነት ስሜት ይኖራችኋል ብዬ አስባለው።

✍️ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ

https://t.me/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም

Send as a message
Share on my page
Share in the group