Translation is not possible.

ሰኞ፣ ማክሰኞ ፣.... ሌላኛው አነጋጋሪው ቪድዬ

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

.

የእስራኤል መንግስት "ሆስፒታሎችን ለምን በቦምብ ታጋያላችሁ?" በሚል ለሚቀርብባቸው ወቀሳ " እናንተ አታዉቁም ሃማስ በየሆስፒታሉ ምድር ዉስጥ የጦር ካምፖች አሉትና ያንን ማጥፋት ስላለብኝ ነው!" የሚል መልስ ሲሰጡ መሰንበታቸው ይታወቃል፡፡ እናም ያንኑ ለወቃሾቻቸው ለማረጋገጥና ለማሳየት በሆስፒታል ዉስጥ ያገኙትን ቀርጸው ይፋ አድርገዋል፣ እናም እያነጋገረ ያለዉም ይሄው በእስራኤል ጦር ይፋ የተደረገው ቪድዬ ነው፡፡

.

ይህ የእስራኤል ወታደር ነው! በጋዛ ዉስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ዉስጥ ግርግዳ ላይ የተለጠፈ ወረቀት ለካሜራ ቀረጻ እያቀረበ ነው፡፡ እንዲህም ይላል

.

"ይህ የምትመለከቱት የአሸባሪዎቹ ዝርዝርና እቅድ ነው፣ እንደምታዩት በአረብኛ የሚለው- እኛ ስምሪት ላይ ነን! ጸረ እስራኤል የሆነው ስምሪታችን ላይ ነን፣ የጀመርነዉም በኦክቶበር 7 ነው! " ይላል ካለ በሁዋላ ቀተል አድርጎ "ይህ የሽብር እቅድ ማስፈጸምያ ሰንጠረዥ ነው፣ እያንዳንዱ አሸባሪ ስሙን ጽፎ ይታያል፣ እያንዳንዱ አሸባሪ የራሱ ፈረቃ አለው....... " እያለ ጠንከር ባለ ግን በሚርገበገብ ድምጽ ያብራራል፡፡

.

ታድያ አለም እየተነጋገረበት ያለው የተባለው ወረቀት ቀረብ ተደርጎ ሲታይ በአረብኛ ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ እሮብ ፣ሃሙስ ... የሚል የሆስፒታሉ የቀን ተቀን መደበኛ ካላንደር ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡

.

ብዙ ሚድያዎች ጉዳዩን እያቀረቡ እየተወያዩበት ሲሆን በተለይ የማህበራዊ ሚድያው የቀኑ ኮከብ ቪድዮ ሆኖ የዋለና ዜማም እስከሚበጅለት ድረስ ብዙዎች የተሳለቁበት ሆኖ አልፏል! .

3 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group