በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
ወላሂ በጣም ልቤን ከሚሰብሩኝ ነገሮች አንዱ ተቸግረው የሰው እጅ የሚያዩ ሰዎችን ማየት ነው።በተለይ ደግሞ ለልጆቻቸው ዳቦ ፍለጋ የወጡ ወላጆችና በሕመም የሚሰቃዩና ለሕክምና የሚውል ገንዘብ የሚጠይቁ ወገኖች ሲኾኑ ከባድ ነው።
የትም አግኟቸው ከያዛችሁት ትንሽዬም ቢሆን ጣል እያደረጋችሁ እለፉ።
ደግሞ በጥሩ ኒያ 5 ብርም ቢሆን ሞባይልህን ተጠቅመህ በአካውንት አስተላልፍ።ብዙዎቻችን ምን ልትፈይድ? እንል ይሆናል።ችግሩ የምንሰጠውን ነገር ዋጋ ማሳጣታችን ነው። ብዙ 5 ብሮች ሲደማመሩ ለተመፅዋች ቁም ነገር ይሆናሉ።የምንሰጠው ለሐብታሙ አላህ ነው።ያ ማለት እሱ ዘንድ ቀና እሳቤና ኢኽላስ ነው ዋናው ነገር።ይሄ ሲባል አላህ ለቀቅ አድርጎልን እያለ በየ ቦታው ሲጠየቅ 100 ብር እንስጥ ማለት አይደለም። 1ብርም እንኳን ከሆነ መስጠት የምትችለው እሷኑ ስጥ ነው።ነቢዩ ከሰደቃ ሁሉ በላጩ የቱ ነው? ተብለው ሲጠየቁ«ደሃ ሰው እየተቸገረም ቢሆን የአቅሚቲ የሚሰጠው ነው።»ብለዋል።
በሌላ ዘገባ ላይ «አንድ ዲርሀም አንድ መቶ ሺ ድርሀምን ቀደመች።»ኣሉ፣ እንዴታ?፣ ሲባሉ፦ «አንድ ሰው ሁለት ዲርሀሞች ነበሩት፣አንዷን ሰደቃ ሰጠ።ሌላ ግለ-ሰብ ግን ከብዙ ንብረቱ አንድ መቶ ሺህ ድርሀም ሰጠ።»ኣሉ።የመጀመሪያው ግማሽ ካፒታሉን ነው የሰጠው፣ሁለተኛው ግን ከብዙ ሀብቱ ነው መቶ ሺህ የሰጠውና።
ሰደቃን አትናቁ።በየ ቦታው ጣል የምታደርጋትን፣በተመፅዋች እጅ ከመድረሷ አስቀድሞ አላህ በቀኝ እጁ ተቀብሎ ያፏፏታል፣የቂያማ ቀንም እጥፍ ድርብ አድርጎ ለባለቤቷ ያቀርባታል ብለዋል።ሰርተን የረሳናቸው ብዙ ወንጀሎች ስላሉብን፣ሰርተን የምንረሳቸው ነገር ግን አላህ የማይረሳቸው ብዙ መልካም ስራዎች ያስፈልጉናል።ሙዕሚን ሁሌም የሚቆጥረው ወንጀሉን ነው፣ሳያውቅ ተጠራቅሞ እንዳያጠፋው በመፍራት። መልካም ስራህማ ልክ ስትሰራው በማይረሳው በጌታህ መዝገብ ስለሰፈረ አታጣውም አያሳስብህ።
ሰደቃ ተቆጥሮ የማያልቅ ትሩፋት ኣለው።
ኻቲማህ እንዲስተካከል፣ከአደጋ እንድትጠበቅ፣ሀጃህ እንዲወጣ፣ከአላህ ቁጣ እንድትድን፣ሐብታም እንድትሆን፣ከበሽታ እንድትፈወስ...በቃ ምን አለፋህ ትሩፋቱ ተዘርዝሮ አያልቅም ሀቂቃ።
አላህ ሆይ ሪዝቃችንን በሐላል መንገድ አስፋልን፣የሰጠሀንን ሐብትም በውዴታህ የሚያወጡ ጀግኖች አድርገን።በሱም ዲንህን ለማስፋፋት፣ባሮችህን ለመንከባከብ ሰበብ አድርገን።
መስጠት ኣኺራንና ጀነትን ለሚመኝ ሙዕሚን ቀርቶ ኢ-አማኒያን ራሱ በሕይወታችሁ ትልቁን ሐሴት የሚሰጣችሁ ነገር ምንድነው? ሲባሉ፣ «የሰዎችን ችግር ፈትቼ ሲደሰቱ ማየት» ሲሉ መስማት የተለመደ ነው።